በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፀን ያገለገለ መኪና እና ልዩ ልዩ አዲስ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2017
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፀን ያገለገለ መኪና እና ልዩ ልዩ አዲስ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ሎት 1 የፌያት ኤንትሬ ሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-07781 ET፣ መኪና፣
ሎት 2 የብሉ በርድ አውቶቡስ መኪና አዲስ መለዋወጫዎች
ሎት 3 የቱርቦ ቻርጀር አውቶቡስ መኪና አዲስ መለዋወጫዎች፣
ሎት 4 ባኮሎደር መኪኖች አዲስ መለዋወጫዎች
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓትአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ ዋና መ/ቤት የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ እና አንድ ኮፒ መታወቂያ ወይም ንግድ ፍቃድ በማስያዝ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ያገለገሉ መኪናና ልዩ ልዩ አዲስ የመኪና መለዋወጫዎች ዘወትር በስራ ሰዓት አዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ ቅጥር ግቢ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የቀረበውን ዋጋ 5% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የማወዳደሪያ ሰነዳቸውን ጨረታ ቁጥሩን /ሎት/ በመግለጽ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
- ጨረታው የሰነድ ሽያጭ ባበቃበት በመጨረሻው 10ኛው ቀን በ5፡00 ሰዓት ተዘገቶ በዚያው ቀን በ5፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ አድራሻ አዋሽ መልካሣ/አዳማ
አዳማ
ስልክ 022 225 0249/022 225 0264
ሞባይል 09 11 734 266/09 11 908 087
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ
ኬሚካል ፋብሪካ
