የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራዝ ለባህር ዳር ሪፈራል ሆስፒታል ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Domestic water pumps and Centrifugal pump ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ቁጥር DCE/SM41/2025
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራዝ ለባህር ዳር ሪፈራል ሆስፒታል ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Domestic water pumps and Centrifugal pump ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
No. |
የዕቃው ዓይነት |
ፕሮጀክት |
የጨረታ |
የጨረታው |
የጨረታው |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
Domestic water |
ለባህር ዳር ሪፈራል |
DCE/SM/41/2025 |
የካቲት 12/2017 ከቀኑ 8:00 |
የካቲት 12/2017 ከቀኑ 8:15 |
50,000 በብር |
ስለሆነም ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፤ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችላቸው ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ (Bid Bond) 120 ቀን ፀንቶ የሚቆይ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋጠ ቼክ (CPO) መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የመድን ድርጅቶች ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
- አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በአንድ ዓይነት ምርት (ብራንድ) ብቻ ነው፡፡ በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ትምህርት ቤት አጠገብ (ቃሊቲ ቶታል አዲሱ ስታዲየም ጀርባ) አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መ/ቤት ግዥ ቡድን
- ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር እና ብዛት መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34
ማዞሪያ 0114-42-22-70/7/72
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ፡- 0114-40-04-71/0114-42-07-46
አድራሻ፡- በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ትምህርት ቤት
አጠገብ (ቃሊቲ ቶታል አዲሱ ስታዲየም ጀርባ) እንገኛለን፡፡
ድረ ገፅ - www.dce.et.com
ኢሜል፡- Info@dce-et.com
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራዝ
