የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ፋ/ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ግልጽ ጨረታ ቁጥር 02/2017 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ፋ/ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ግልጽ ጨረታ ቁጥር 02/2017
- የጽሕፈት መሣሪያዎች (ሎት 01)፣
- የፅዳት ዕቃዎች (ሎት 02)፣
- የደንብ ልብስ (ሎት 03)፣
- ቋሚ ዕቃዎች (ሎት 04)፣
- ህትመት፣ የተለያዩ ኮምፒውተሮች፣ ፎቶ ኮፒና ፕሪንተር እና ላፕቶፕ ጥገና (ሎት 05) ስለሚፈልግ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም መጫረት የምትፈልጉ ፡-
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለበት፡፡
- በዘርፉ የተሰማራ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈለበት ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ፡፡
- የግብር ኮድ መለያ ቁጥር /TIN/ ሰርተፍኬት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነበት ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ እንዲሁም በጥቃቅን የተደራጁ ለሚወዳደሩበት ሎት (የዕቃ ዓይነት) እራሱ ማህበሩ አምራች ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ ያለውና (TOT) ተመዝጋቢ የሆኑበት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት (01) ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ)፣ ለሎት (02) ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ)፣ ለሎት (03) ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ)፣ ለሎት (04) ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ) ለየብቻው (በየሎቱ) በባንክ የተረጋገጠ CPO (ሲፒኦ) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሎት (05) ላይ ለሚወዳደሩ CPO (ሲፒኦ) ማስያዝ አይጠበቅባቸውም፡፡
- የጨረታ አሸናፊዎች ባሸነፉት እቃ ብር መጠን የውል ማስከበሪያ 10% በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ አለበት
- ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዛው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ውክልና ያላቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በመንግሥት ተቋም በጥቃቅን ለተደራጁ ሰነድ በነፃ እንዲወስዱ ከተደራጁበት መ/ቤት የተፃፈላቸውን ደብዳቤ ኦሪጅናል ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የመወዳደሪያ ሀሳብ ፋይናሻልና ቴክኒካል ሁለት በታሸገ ፖስታ ኮፒ እና ኦርጅናል በማድረግ ፋ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የተዘጋጀው ጨረታ ዝርዝር ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ከመሥሪያ ቤቱ በአካል(በውክልና) ቀርቦ መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉትን እቃዎች በራሱ ወጪ እስከ መሥሪያ ቤቱ መጋዘን ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው::
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 1 አስተዳደር ልዩ ቦታ ኮተቤ 02 አለፍ ብሎ ደጃዝማች ወንድራድ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ፊት ለፊት 1ኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገዎ በስልክ ቁጥር 011-6–50-80-50
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ፋይናንስ ጽ/ቤት
