የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በ2017 የበጀት ዓመት ለክልሉ ፖሊስ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
Oromia Police Commission (የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን)
የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በ2017 የበጀት ዓመት ለክልሉ ፖሊስ ስራ አገልግሎት የሚውሉ
የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ግዥ፣
የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች፣
የውሃ መስመር ዝርጋታ እና ጥገና የሚውሉ ዕቃዎች ግዥ እና
የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና የሚውሉ ዕቃዎች ለመግዛት በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ፖሊስ ኮሚሽኑ የሚገዛቸው ዕቃዎች ከዚህ በታች በሎት ተለይተው ቀርበዋል፡፡
በዚሁ መሰረት የግዥው አይነት፡-
ሎት አንድ፡- የተለያዩ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ግዥ
ሎት ሁለት፡- የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች፣ የውሃ መስመር ዝርጋታ እና ጥገና የሚውሉ ዕቃዎች ግዥ
ሎት ሶስት፡- የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና የሚውሉ ዕቃዎች ግዥ
በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩ ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪዎችን ለውድድር ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ የ2017 የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ስለመክፈላቸው የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተወዳዳሪ ለሚወዳደሩበት ዕቃ አንዳንድ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተወዳዳሪ የመወዳደሪያ ሰነድ ሲያዘጋጅ እና ሲያስገባ የየሎቱን ለየብቻ ማቅረብ አለበት፡፡ ሁሉንም ወይም ሁለት ሎት በአንድ ሰነድ በማዘጋጀት የሚያቀርብ ድርጅት ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2% ሆኖ የሚያስዙት ዋስትና ከ500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይጠበቅባችዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 (አስራ አምስት) ቀናት ከፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- አሽናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎችን በራሱ ወጪ የማጓጓዣ መጫኛ እና ማዉረጃ ወጪዎችን ሸፍነው በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ግምጃ ቤት ድረስ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎችን ታክስ እንዲሁም ትራንስፖርት እና የመጫኛ እና ማውረጃ የጉልበት ማንኛውንም ወጭን ጨምሮ መሙላት አለበት ይህ ካልሆነ ግን የቀረበ ዋጋ ወጪ አካቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀነ ገደብ 14/6/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይሆናል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 14/06/2017 ዓ.ም በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የመሰብሰቢያ አደራሽ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አ/አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ላንቻ አካባቢ
ለተጨማሪ መረጃ፡- 0913 108 990 ወይም 0996 054 778 መደወል ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን
