ደቡብ ኢትዮጵያ ክ/መ/ በወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በሴፍትኔት ካፒታል የ10,000 ሜ.ኪ ኩሬ ቁፋሮ በሆቢቻ ቦንጎታ ቀበሌ እና በጭፍሳ ቀበሌ በግልጽ- ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት ሆቢቻ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር-PNSP-(001/2017)
ደቡብ ኢትዮጵያ ክ/መ/ በወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በሴፍትኔት ካፒታል የ10,000 ሜ.ኪ ኩሬ ቁፋሮ በሆቢቻ ቦንጎታ ቀበሌ እና በጭፍሳ ቀበሌ በግልጽ- ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ፡-
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ TIN ሠርተፍኬት ያለው አቅራቢነት ምዝገባ ም/ወረቀት ያለው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፤ ምዝገባ ም/ወረቀት ያለው እና የግብር ግዴታቸውን ስለመውጣታቸው ማስረጃ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር ድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎች ጽ/ቤት መምሪያ ያፃፈ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ደረጃ wwC-5 እና ከዛ በላይ መሆን አለበት፡፡ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የመልካምሥራ አፈጻጸም ከሥራው ጋር ተያያዥነት ያለው ቢያንስ ሶስት የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የሳይት ምልከታ ካስፈለገ ለግብርና ጽ/ቤት ደብዳቤ በመፃፍ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር 20,000 ብር (ሃያ ሺህ ብር ብቻ) መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበረያ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሠነድ ኦርጅናሉንና ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሽገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውንና የፕሮጀክቱን ስም በመጥቀስ የአንዱን ዋጋ በመጥቀስ በትክክል በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታው ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 350 (ሶስት መቶ ሃምሳ ብር ብቻ) በመክፈል ከሆቢቻ ወረዳ ፋይ/ጽ/ ቤት በአካል በመቅረብ ንግድ ፍቃድ በማሳየት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 21 /ሃያ አንድ/ ስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በዕለቱ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ሰዓት ሆቢቻ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ግ/ፋይ/ዋና የሥራ ሂደት አዳራሽ ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው ከሆነ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በዞኑ ወይም በወረዳ ውስጥ ከዚህ በፊት ምንም ዓይነት ማስጠንቀቂያ ያልተፃፈበት መሆን አለበት፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች የመወዳደርያ ሀሳብ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ /ራሳቸውን ከጨረታው ማግለል አይቻልም፡፡
- ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማመልከቻ በመጻፍና ሳጥን ውስጥ በማስገባት ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ አገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ -- 091 008 9560/ 093 133 1035
ወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት ሆቢቻ
