በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ መንግስት የካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለዴቻ ወረዳ ቀሺ ማዘጋጃ ቤት በኩል በውስጥ ገቢ በጀት ለቀሺ ከተማ ህዝብ አገልግሎት የሚሰጥ ግንባታን በየሎት በማከፋፈል ቄራ ግንባታና ኮንቲነር ሼድ ግንባታ ሥራ በየሎት በማከፋፈል ህጋዊ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
- በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ መንግስት የካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለዴቻ ወረዳ ቀሺ ማዘጋጃ ቤት በኩል በውስጥ ገቢ በጀት ለቀሺ ከተማ ህዝብ አገልግሎት የሚሰጥ ግንባታን በየሎት በማከፋፈል ቄራ ግንባታና ኮንቲነር ሼድ ግንባታ ሥራ በየሎት በማከፋፈል ህጋዊ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 01 - የቄራ ግንባታ፣
- ሎት 02 - ኮንቲነር ሼድ ግንባታ፣
- በዚህም መሰረት ደረጃ 7BC/GC እና ከዛም በላይ የግንባታ ፈቃድ ያለው፤ በ2017 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፤ የተ/እ/ታ (ቫት) ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ምስክር ወረቀት እንዲሁም በመንግስት ግዥ ጨረታ በ BC/GC ግንባታ ስራ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ሁሉ በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ 2015/2016 ዓ.ም በጥራት ሰርቶ ስላስረከቡት በ BC/GC ግንባታ የመልካም ስራ አፈጻጸም ደብዳቤ ወይም የምስክር ወረቀት ያላቸው፤ በተጨማሪ ከፍያ የተፈጸመበትን የቫት ደረሰኝ ማቅረብ የምችሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ በሥራ ቀናት በሥራ ሰዓትብቻ እስከ 28ኛው ቀን ድረስ ለወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት በየሎቱ የማይመለስ 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከመ/ቤታችን ግዥ ኬዝ ቲም ሰነድ በመውሰድና በዝርዝሩ መሰረት ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመውሰድ ከተ/እ/ታ (ቫት) ጋር በመሙላት እንዲሁም ከላይ የተዘረዘሩ የንግድ ፈቃድና ተያያዥ የመረጃ ኮፒዎችንና የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በአንድ ፖስታ በማሸግ ዋጋ የተሞላበትን ኦሪጅናልና ኮፒውን የጨረታ ሰነድ በሌላ ፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠሩ ተከታታይ በሥራ ቀናት እስከ 28ኛው ቀን ሎት 01 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡ ለሎት 02 በዕለቱ በ29ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ሎት 1 በዕለቱ 8:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል፡፡
- ሎት2 በዕለቱ 8:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 01 ብር 20,000.00/ሃያ ሺህ ብር/ ብቻ ለሎት 02 ብር 20,000.00/ሃያ ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ አከፋፈት ወቅት የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ሂደት አያስተጓጉለውም።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-23-33-75-68 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ መንግስት የካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
