በ2017 በጀት ዓመት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በወላይታ ዞን የኦፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው የሚገኙ በተለያዩ ጊዜያት በግዥ፣ በዕርዳታ እና በስጦታ ያገኟቸውን ሞተር ሳይክሎች፣ ጄኔሬተሮች፣ የውሃ ታንከሮች፣ የእርሻ መሳሪያዎች (WalkingTractor)፣ አሮጌ ጎማዎች፣ የቧንቧ ብረቶች እና መጽሐፍቶች በግልጽ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በወላይታ ዞን ኦፋ የወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ያገለገሉ ንብረቶች ለመሸጥ የወጣ ሐራጅ
ጨረታ ማስታወቂያ
በ2017 በጀት ዓመት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በወላይታ ዞን የኦፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው የሚገኙ በተለያዩ ጊዜያት በግዥ፣ በዕርዳታ እና በስጦታ ያገኟቸውን ሞተር ሳይክሎች፣ ጄኔሬተሮች፣ የውሃ ታንከሮች፣ የእርሻ መሳሪያዎች (WalkingTractor)፣ አሮጌ ጎማዎች፣ የቧንቧ ብረቶች እና መጽሐፍቶች በግልጽ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች
- ማንነቱን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ እና የጨረታ ሰነድ የገዙበት ደረሰኝ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከላይ የተገለጹ ያገለገሉ የመንግስት ንብረቶችን ዝርዝር የያዘውን የመወዳደሪያ ሰነድ በኦፋ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20% (ሃያ በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰአት ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ሌሎች ታዛቢዎች በተገኙበት በኦፋ ወረዳ ጉታራ አዳራሽ ውስጥ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ እንደተረጋገጠ ያሸነፈበትን ዋጋ በኦፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ባንክ አካውንት ሙሉ በሙሉ ገቢ ሲያደርግ ያሸነፈውን ንብረት ወዲያውኑ ይረከባል። ሌሎች ዝርዝር ሰነድ የሚካተቱ ይሆናል፡፡
- አሸናፊ በሆኑበት በርካታ ያገለገሉ የተለያዩ ንብረቶች እና ያገለገሉ ሞተር ብስከሌቶች ሽያጭ በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ስምምነት ውል ለመግባት ፍቃደኛ ካልሆነ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- የተሽከርካሪዎችን የስም ዝውውር እና ህግ የሚጠይቃቸውን ማንኛውንም ክፍያዎች (ወጪዎች) አሸናፊው የሚሸፍን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት ዕለት ጀምሮ ለጨረታ የቀረቡ ያገለገሉ ንብረቶችን በኦፋ ወረዳ ባሉበት ቦታ በመገኘት በሥራ ሰዓት ማየት ይችላሉ፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፦ 046 469 0420 ወይም 0913 851 344 ደውለው መነጋገር ይችላሉ፡፡
በወላይታ ዞን ኦፋ የወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
