ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ለዋና መ/ቤት ለአስተዳደራዊና ለፕሮጀክት ለሚያስፈልጉ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት ዕቃ፣ የኤሌክትሪከ ዕቃ፣ ፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ቀለም፤ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ጎማና ባትሪ እና የቧንቧ ዕቃዎች አቅራቢ በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Ethio Engineering Group (ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ)
የግዥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩኘ
የጨረታ ቁጥር፡- ኢ.ኢ.ግ/ሰቼማ ብግጨ /2017/004
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ለዋና መ/ቤት ለአስተዳደራዊና ለፕሮጀክት ለሚያስፈልጉ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት ዕቃ፣ የኤሌክትሪከ ዕቃ፣ ፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ቀለም፤ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ጎማና ባትሪ እና የቧንቧ ዕቃዎች አቅራቢ በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
-
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቶች የግብር መክፈያ ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥና በግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ቅጂ ፤ በበጀት ዓመቱ ዘርፉ ላይ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ቅጂ የንግድ ስም ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት፤ በመንግስት ግዥ ኤጄንሲ ድረ ገፅ (www.ppa.gov.et) በአቅራቢነት የተመዘገቡበት ማስረጃ እና የግብር መክፈያ መለያ ሰርተፍኬት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስም በሂሳብ ቁጥር 1000028606177 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ዋና መስሪያ ቤት (አዲስ አበባ ሜከሲኮ ከሚገኘው ከፌደራል ፖሊስ ዋና መ/ቤት ዝቅ ብሎ ከኦላ ማደያ አጠገብ) በመቅረብ ከግዥ ክፍል ሰነዱን በሶፍት ኮፒ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለዕቃው ሽያጭ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡
- ጨረታውን በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይየሚቆይ ሆኖ በ16ኛው የግሩፑ የስራ ቀን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ 2ኛ ወለል መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ግሩፑ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ሰኘላይ ቼይን ማኔጅመንት መምሪያ ግዥ ቡድን ኢትዮ ኢንጂነሪንግ
