Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የሚዳ ወረሞ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
  • Address አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 011 117 05 44
  • Website
  • Deadline11 Feb 2025, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በአማራ ክልል በሰሜን ሽዋ ዞን በሚዳ ወረሞ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለተቋሙ አገልግሎት የሚውል ለ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን 1ኛ የፅህፈት መሳሪያዎች 2ኛ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች 3ኛ የህትመት ስራዎች 4ኛ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 5ኛ የፅዳት እቃዎች 6ኛ ፍራሽና ብርድ ልብስ 7ኛ የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች 8ኛ የውሃ እቃዎች 9ኛ የፕሪንተር ቀለም 10ኛ የግንባታ እቃዎች 11ኛ ፈርኒቸር 12ኛ የማሽነሪ ጥገና በግልፅ ጨረታ ማስታወቂ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የሚዳ ወረሞ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ክልል በሰሜን ሽዋ ዞን በሚዳ ወረሞ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለተቋሙ አገልግሎት የሚውል ለ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን 1ኛ የፅህፈት መሳሪያዎች 2ኛ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች 3ኛ የህትመት ስራዎች 4ኛ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 5ኛ የፅዳት እቃዎች 6ኛ ፍራሽና ብርድ ልብስ 7ኛ የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች 8ኛ የውሃ እቃዎች 9ኛ የፕሪንተር ቀለም 10ኛ የግንባታ እቃዎች 11ኛ ፈርኒቸር 12ኛ የማሽነሪ ጥገና በግልፅ ጨረታ ማስታወቂ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. በ2017 ዓ.ም በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ እንዲሁም በጨረታ ሰነድ ላይ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር ከብር 200000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ስዓት በተከታታይ ለዕቃ አቅርቦት እስከ 15 ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ 100 /መቶ ብር/ በመክፈል በሚዳ ወረሞ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን በመገኘት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የነጠላ እና የጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር ተሞልተው ኮፒ እና ኦርጅናል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ባንኮች የሚሰጥ 2% ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይንም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በጥሬ ገንዘብ ወይም በገቢ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ከማንኛውም ከተፈቀደለት ባንክ የሚቀርብ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ ...CPO በአማርኛ ተተርጉሞ በአባሪነት ማቅርብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በአዲሱ የንግድ ስራ መስጫ መደብ እና የተሰማሩበት የንግድ ስራ ፍቃድ መስጫ ኮድ ቁጥር፣ የንግድ ስራ ፍቃድ መስጫ መደብ እና የተሰማሩበት የስራ መስኮች በተገለፀው ትንታኔ የተፃፈው ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
  6. ተጫራቾች የዕቃውን ዋጋ በዝርዝርና በጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስም ፣ ፊርማና ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ በሚዳ ወረሞ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታው ተጫራቾች በአካልም ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በሚዳ ወረሞ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ዕቃውን በሚዳ ወረሞ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በሚገኘው ንብረት ክፍል ግቢ ውስጥ ማድረስ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች በተቀመጠላቸው ከፍት ቦታ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር ሞዴል፣ብራንድ /መለያ/ የተመረተበትን ሀገር በሚነበብ ፅሁፍ (ግልጽ በሆነ ፅሁፍ) አካቶ በትክክል መሙላት አለበት፡፡
  10. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ጥራት ያለውና ኦርጅናል እቃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 011 117 05 44 / 011 117 05 54 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የሚዳ ወረሞ

የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

 

Save Tender