Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ
  • Address ወልቂጤ ከተማ መብራት ኃይል ፊት ለፊት ፈድሉ ህንጻ : በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-3-65-82-88
  • Website
  • Deadline10 Feb 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Pumps, Motors And Compressors

የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የውሃ መሳቢያ ፓንፕ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የውሃ መሳቢያ ፓንፕ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ  የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡-

  1. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  3. በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ማንኛውም ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ፡
  4. የተዘጋጀ ጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከመ/ቤቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንሻል የጨረታ ሰነድን ለብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለእያንዳንዱ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኤንቨሎፑ የውጭ ገጽ ዋና /ኦሪጅናል) ወይም ኮፒ ብሎ በመጻፍ አሽገው ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ከ8፡00 ሰዓት በፊት ብቻ ይሆናል። ጨረታው በ15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8፡30 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም 15ኛው የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋው እና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ በግልጽ ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለውሃ መሳቢያ ፓንፕ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ CPO ፣ ቼክ ፣ ባንክ ጋራንቲ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  8. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር 011-3-65-82-88 ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ ፡-

መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የመ/ቤቱ አድራሻ:- ወልቂጤ ከተማ መብራት ኃይል ፊት ለፊት ፈድሉ ህንጻ

 

የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ

 

Save Tender