Tender Detail

Tender Details

  • Company MIDROC INVESTMENT GROUP (ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ)
  • Address አዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሸገር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቢሮ ቁጥር 04, Phone: +251913953038
  • Websitehttps://www.midrocinvestmentgroup.com/
  • Deadline05 Feb 2025, 10:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Machinery Spare Parts

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ስር ካሉ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የማሽነሪ የመለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር መሸጥ ይፈልጋል፡፡

MIDROC INVESTMENT GROUP (ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ)


 

MIDROC INVESTMENT GROUP

የማሽነሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎች

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር -Disposal 0003/2017

 

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ስር ካሉ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የማሽነሪ የመለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት፡-

  1. በጨረታ የሚሳተፍ ድርጅት/ግለሰብ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  2. ተጫራቾች አዲስ አበባ የካ አባዶ ገደራ አካባቢ በሚገኘው በዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ቁጥር 7 በአካል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በተጠቀሰው ድርጅት ስም በዳሽን ባንክ የሂሳብ ቁጥር 0025009238018 በማስገባት ያስገቡበትን ደረሰኝ በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራች በጨረታው ለሚሳተፍባቸው መለዋወጫዎች ለጨረታ ያቀረቡትን አጠቃላይ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚፈልጓቸውን የመለዋወጫ ዓይነት ድርጅቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስ እንዲሁም ከሲፒኦ ጋር በማካተት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ አስረኛው ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ድረስ በዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ቁጥር 7 ለመረጡት መለዋወጫ ፋይናንሻል ፕሮፖዛላቸውን በታሸነ ኤንቨሎፕ በማዘጋጀት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ፤ ጨረታው በዕለቱ 4:45 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች አዲስ አበባ በዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ቁጥር 7 ቅጥር ግቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት አስር የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መለዋወጫዎችን ማየት ይችላሉ፡
  6. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ግለሰብ (ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለጸለት በ6 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን መለዋወጫ ሙሉ ዋጋ ገቢ በማድረግ ማንሳት ሲኖርበት ማንሳት ካልቻለ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው CPO እንዲወረስ ይደረጋል፡፡
  7. በጨረታው የተሸነፈ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ CPO ለተጫራች እንዲመለስ ይደረጋል። ግሩፑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሠረዝ ህጋዊ መብት አለው፡፡

 

አድራሻ

አዲስ አበባ

ለሚኩራ ክፍለ ከተማ

ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ቁጥር 7

ማሳሳቢያ፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 913 953038 +251 911 219704 ደጠቀሙ።

 

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ

 

Save Tender