የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የሚፈልጋቸውን ሎት 1- ፕላስቲክ የውኃ ማስተላለፊያ ቱቦ (HDPE Pipes)፣ ሎት 2- የብየዳ ጀኔሬተር (ዌልዲንግ ጀኔሬር)፣ ሎት 3- የደንብ ልብስ እና ሎት 4- የውኃ ማጣሪያ ኬሚካል (ኮፐር ሳልፌት) በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የሚፈልጋቸውን ሎት 1- ፕላስቲክ የውኃ ማስተላለፊያ ቱቦ (HDPE Pipes)፣ ሎት 2- የብየዳ ጀኔሬተር (ዌልዲንግ ጀኔሬር)፣ ሎት 3- የደንብ ልብስ እና ሎት 4- የውኃ ማጣሪያ ኬሚካል (ኮፐር ሳልፌት) በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መረጃዎች በማቅረብ በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
- የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት (TIN) ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ /VAT Register/ የሆኑና
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ የተመሰከረለት ህጋዊ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ማስያዝ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ /በመክፈል ጎ/ከ/ው/ፍ/አገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 27 በመግዛት በጨረታ ዝርዝሩ መሰረት ዋጋቸውን በመሙላትና በፖስታ በማሸግ ከ21/05/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ቀን 05/06/2017 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 14 ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች የተወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ተለያይቶ በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል /ቴክኒካልና ፋይናንሻል/ እና አንድ ኮፒ /ቴክኒካልና ፋይናንሻል/ የያዙ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ጨረታው ከ21/05/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 05/06/2017 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል። ጨረታው በተመሳሳይ ቀን በ05/06/2017 ዓ/ም በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታው መከፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። በአገር አቀፍ በዓላት ካልተዘጋ በስተቀር ዘወትር ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት የስራ ቀን ሲሆን ይህም እንደ አንድ የስራ ቀን ይቆጠራል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 211 3316/ 058 112 0697 በመደወል ማነጋገር ይችላሉ።
በጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር
