በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያቤቶች የሚሆን ለአስፋዲን ቀበሌ ጉዋን ምንጭ በቦታው ግንባታ፣ ጠይባ ቀበሌ አመዴ ምንጭ በቦታው ግንባታ፤ አመቶ ቀበሌ አዲስ ምንጭ በቦታው ዘሏን ስፋቶ ቀበሌ ከነባር የውሃ ተቋም ማስፋፊያ ስራ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር GGWW/021/2017
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያቤቶች የሚሆን ለአስፋዲን ቀበሌ ጉዋን ምንጭ በቦታው ግንባታ፣ ጠይባ ቀበሌ አመዴ ምንጭ በቦታው ግንባታ፤ አመቶ ቀበሌ አዲስ ምንጭ በቦታው ዘሏን ስፋቶ ቀበሌ ከነባር የውሃ ተቋም ማስፋፊያ ስራ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች:-
- የዘመኑ ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡
- የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC / WC ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ የሆነ ተቋራጮች
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ሰአት ድረስ የማይመለስ ብር 300 / ሶስት መቶ ብር ብቻ / በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀልአምባ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ /ቤት ስም ማሰራት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሲያቀርቡ ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማደረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በማሸማ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በማሸግ ቴክኒካል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሀያ አንድ) ተከታታይ ቀናት መሀልአምባ የገ/ጉ/ወ/ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ተከታታይ ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ሰነድ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
ማሳሰቢያ
- በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም።
- በወረዳው ውስጥ አንድም ፕሮጀከት የያዘ አካል መወዳደር አይችልም።
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከአሰሪው መስሪያ ቤት የሳይት ምልከታ ማየታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
- አሸናፊው ድርጅት ቅድመ ክፍያ ሳይወስድ ሳይጠይቅ ስራ መጀመር የሚችል።
ለበለጠ መረጃ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ
ስልክ ቁጥር 0113360162/146 ደደውሉ
መሀል አምባ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
