Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline14 Feb 2025, 2:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ 1 ጠቅላላ ስራ እና የህንፃ ስራ ተቋራጭ (GC -1/BC-1) የሆኑ የሃገር ውስጥ ጨረታ ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው የሃገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ የነቀምትና ደምቢዶሎ ኤርፖርቶች የመንገደኞች ማስተናገጃ እና ተያያዥ ሕንፃዎችን ዲዛይን እና ግንባታ ጨረታ (Design and Build of Passenger Terminals and Support Facility Buildings at Nekemte and Dembidolo Airports) ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ፡- SSNT-T 525

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ደረጃ 1 ጠቅላላ ስራ እና የህንፃ ስራ ተቋራጭ (GC -1/BC-1) የሆኑ የሃገር ውስጥ ጨረታ ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው የሃገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ የነቀምትና ደምቢዶሎ ኤርፖርቶች የመንገደኞች ማስተናገጃ እና ተያያዥ ሕንፃዎችን ዲዛይን እና ግንባታ ጨረታ (Design and Build of Passenger Terminals and Support Facility Buildings at Nekemte and Dembidolo Airports) ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ የሚያገለግል ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277 (E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T525 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለሁለቱም ፕሮጀክቶች የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ አምስት መቶ ሺህ ብር (500,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቋም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንከ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ150 ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡ አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው::

የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ ለእያንዳንዱ ፕሮጀክት ሥራው ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ 730 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ የካቲት 07 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ9:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ:- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር፡- 011-5-17-80-25

ኢ-ሜይል:- WoldeM@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

Save Tender