በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሚያሰራው የመሀል አምባ መናኸሪያ፣ የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ አጥር ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሃገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር: GGWW/0019/2017
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሚያሰራው የመሀል አምባ መናኸሪያ፣ የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ አጥር ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ፡-
- የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ፣ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/BC ደረጃ 8 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቋራጮች፤
- በጨረታው ለመወዳዳር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙትን ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆነ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው::
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀል እምባ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሲያቀርቡ ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴከኒካል በሚል በመለየት፣ ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ ከባንኪ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦሪጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በማሸግ ቴክኒካል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት መሀል አምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ተከታታይ ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- በጨረታው ሰነድ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
ማሳሰቢያ ፡-
- በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም፡፡
- በወረዳው ወስጥ አንድም ፕሮጀክት የያዘ አካል መወዳደር አይችልም፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከአሰሪው መስሪያ ቤት የሳይት ምልከታ ማየታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ቅድመ ከፍያ ሳይወስድ/ ሳይጠይቅ ስራ መጀመር የሚችል፤
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 011-3-36-01-62/146 ደደውሉ፡፡
የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ
