በሲ/ብ/ክ/መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ የስ/ሂደት ከየካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለ6 (ለስድስት) ተከታታይ ወር የሚቆይ ለህግ ታራሚዎች የምግብ ማብሰያ ማገዶ እንጨት ግዥ ለመፈጸም ከዚህ በታች የተመለከቱትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም ግዥ/ፋይ/ን/አስ/የስ/ሂደት
ለህግ ታራሚዎች ምግብ ማብሰያ ማገዶ እንጨት
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ ቁጥር፡-03/2017
በሲ/ብ/ክ/መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ የስ/ሂደት ከየካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለ6 (ለስድስት) ተከታታይ ወር የሚቆይ ለህግ ታራሚዎች የምግብ ማብሰያ ማገዶ እንጨት ግዥ ለመፈጸም ከዚህ በታች የተመለከቱትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
መለኪያ |
ምርመራ |
|
1 |
የማገዶ እንጨት ከባህር ዛፍ፣ ከብርብራ፣ አቡካቶ ወይም በማረሚያ ተቋም ተቀባይነት ያገኘ እንጨት ጭራሮ የሌለው እንጨት የተዘጋጀ ሆኖ ሲለካ 1ሜX1ሜX1ሜ የሆነ |
በሜትር ኩብ |
|
|
2 |
በግንዲላ የተዘጋጀ የማገዶ እንጨት ሆኖ ለዳቦ ቤት የሚሆን ከባህር ዛፍ፣ ከብርብራ፣ አቡካቶ ወይም በማረሚያ ተቋም ተቀባይነት ያገኘ እንጨት |
በሜትር ኩብ |
|
ህጋዊ ተወዳዳሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ፡- ጨረታው የሚካሄድበት የሥራ ቋንቋ አማርኛ ሲሆን በሚወዳደሩበት የንግድ ሥራ ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይነት ማስረጃ ያላቸው፤ የዘመኑን የግብር የከፈሉና ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ፤ በጨረታ መወዳደር የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉና በአቅራቢነት ዝርዝር ለመመዝገባቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የያዘ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉና በጨረታ የተጠቀሱ መሥፈርቾችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአሥራ አምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሠነድ ከይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም ግዥ/ፋይ/ን/አስ/የስ/ሂደት ክፍል ውስጥ ገዝተው ከሞሉ በኋላ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ አሥራ አምስተኛ ቀን 11፡10 ሰዓት ድረስ የታሸገውን ኢንቨሎፕ ወደ ጨረታ ሳጥን አስገብተው በዚሁ ቀን 11፡15 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ከታሸገ በኋላ በዕለቱ 11፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም ይከፈታል፡፡ የጨረታውን ሰነድ ለውድድር አቀርበው ከግል ፍላጎታቸው /ሁኔታ/ የተነሳ በዕለቱ የማይገኙ ሲሆን ጨረታው ተከፍተው ውጤቱ ይገለጽላቸዋል እንጂ የጨረታውን ሂደት የሚያስተጓጉል ነገር አይኖርም፡፡ አንድ ተጫራች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡ በጨረታው ሠነዱ የተመለከቱትን ዓይነቶች ከላይ በሰንጠረዥ ውስጥ በተገለጸው መሰረት ይሆናል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸ ጊዜ ጅምሮ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ አቅርበው ውል መፈጸም አለባቸው፡፡ አሸናፊዎችን አሸናፊነታቸው እንደተገለጸ ውል የማይፈጽሙ ከሆነ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ አይመለስም (ይወረሳል)፡፡ የጨረታው ዝርዝር በጨረታው የአፈጻጸም መመሪያ ላይ የተገለጸ ስለሆነ በይበልጥ ተቀባይነት ያለው የጨረታ ሰነድ በመሆኑ አንድ በአንድ ማንበብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታ አውጪው መ/ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046-2-25-24-03 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም ግዥ/ፋይ/ን/አስ/የስ/ሂደት
