በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አገልግሎት የሚውል ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ (Sidama National Regional Government Government Communication Affairs)
በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጉዳዩ፡- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽሕፈት መሣሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድረው ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አገልግሎት የሚውል ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ፡-
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምዝገባ ወረቀት የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆነው የግዜ ገደብ የሚገልጽ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማስረጃ በመያዝ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ሰነድ በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛ የሥራ ቀናት ውስጥ ቦታ በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት ፕሬስ ሴክረተሪያት ግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 416 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ የውል ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በማዘጋጀት ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቬሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታ መመሪያ ጋር አባሪ ተደርጎ ተያይዟል፡፡
- ይህ ጨረታ በ10ኛው በሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 10ኛው ቀን ቅዳሜና ዕሁድ ወይም በዓል ከሆነ የጨረታ መክፈቻ ዕለት በተጠቀሰው ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- አቅራቢዎቹ የእቃ ዝርዝር ማቅረቢያ ፎርም ላይ ነጠላ ዋጋውን እና ጠቅላላ ዋጋውን እንዲሁም ቀን፣ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ማሳረፍ ይገባቸዋል፡፡ አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች መመሪያ ባለማከበራቸው የሚፈፀም ማንኛውም ስህተት ኃላፊነቱ የተጫራቾች ይሆናል።
- አቅራቢዎች ጠቅላላ ዋጋ በቁጥርና በፊደል መጻፍ አለባቸው፡፡ በቁጥርና በፊደል በተገለጸው የዋጋ መጠን መካከል አለመመጣጠን ካለ በፊደል የተገለጸው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካል ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
* አድራሻ ፡-በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 416
ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
