Tender Detail

Tender Details

  • Deadline08 Feb 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሐረርጌ ቅርንጫፍ ድንድን ዲስትሪክት ላይ የሚገኘውን አሮጌ ብረታብረትና ሌሎች ያገለገሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ

የአሮጌ ብረታብረት ሽያጭ ጨረታ

ማስታወቂያ ቁጥር OFWDH/MM-01/2017

 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሐረርጌ ቅርንጫፍ ድንድን ዲስትሪክት ላይ የሚገኘውን አሮጌ ብረታብረትና ሌሎች ያገለገሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ፡-

    1. የብረታብረት እና ተዛማጅ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፤ የቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያለው ድርጅት ወይም ግለሰብ በጨረታው መወዳደር ይችላል። ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጭሮ ከተማ ምዕራብ ሀረርጌ ዞን ውሃ ልማት ግቢ ውስጥ ከሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሐረርጌ ቅርንጫፍ ቢሮ ቁጥር 2 ወይም ቀበና ሼል /ኦይል ሊቢያ/ አጠገብ ከሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
    2. ተጫራቾች ለጨረተ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) የሚሆን ባቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ለምትጫረቱ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች፤ በድርጅቱ ሐረርጌ ቅርንጫፍ ለምትጫረቱ ጭሮ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
    3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ጨረታው ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ባሉበት ይከፈታል።
    4. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251255512239 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ

ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሐረርጌ ቅርንጫፍ

 

Save Tender