በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ እና ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚውል እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ፑል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ እና ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚውል
- የቋሚና አላቂ ዕቃዎች፣
- ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- ፈርኒቸር፣
- የሳይክል ጎማ ስለሚፈልግ በውስን ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- ተጫራቾች 200,000.00 በላይ ከሆነ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊክሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
- ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ፋይናንሽያል ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት ለየብቻው በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 400.00(አራት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ኦሪጅናል የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ እና ኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት ቢሮ በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 1-12 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ለተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ21ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር L-12 በግልጽ ይከፈታል፡፡ በዚህ ቀን ያልተኙ ተጫራቾች የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉሉም፡፡ ነገር ግን 21 ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1-12 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ መጠየቅ (መረጃ መላክ ይችላሉ)፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገም ስልክ ቁጥር፡- 058-2-20-79-40/058-2-26-14-39
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ፑል
