በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ኢ/ጽ/ቤት ለኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት አገልግሎት የሚሆን Canon 5D ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መ/በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ኢ/ጽ/ቤት ለኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት አገልግሎት የሚሆን cam ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለይ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለሞተሮቹ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በምስ/አዘ/በር/ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ።
በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የቫት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ /CPO/ 15,000 ብር ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉበትን እቃ ምስ/አዘ/በ/ወ/ፋ/ኢ/ጽ/ቤት ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ የትራንስፖርት የማስጫኛና የማውረጃ ጨምሮ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አንዱ ባቀረበው ዋጋ ተንተሪሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣ በ15ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
- በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ ፋይናንሻል ዋጋዎች በግልጽና በጥራት የሚታዩና ስርዝ ወይም ድልዝ ያልሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሚፈልጉት ዕቃ ላይ መወዳደር ይችላሉ፤ ሆኖም ለአንድ እቃ ከተጠየቀው ብዛት አሳንሶ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ወረዳው ከአዲስ አበባ ርቀቱ 221 ኪሎ ሜትር ሲሆን 176 ኪሎ ሜትር አስፓልት እና 45 ኪሎ ሜትር ፒስታ መንገድ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 21 33 86 96 /09 33 62 02 20
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መ/በስልጤ ዞን የምስራቅ
አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
