Tender Detail

Tender Details


የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የቅየሳ መሳሪያ (Total station) ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ ብግጨ /ዕግ/32/04/2017 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር :- FHC/NCB/PG/32/04/2017

 

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የቅየሳ መሳሪያ (Total station) ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ ብግጨ /ዕግ/32/04/2017 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ፡-

  1. ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የቅየሳ መሳሪያ (Total station) ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውንና የዕቃውን ዋጋ በተለያዩ በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞከራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የግዥ መመሪያ መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው ዋና መ/ቤት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ወይም ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ሲፒኦ (CPO) በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  5. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር :- 011-8-55-30-35 ወይም 011-5-53-95-35

ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን

Save Tender