የወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ ዓይነት ህትመቶችን ለማሳተም ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ ዓይነት ህትመቶችን ለማሳተም ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነድ (ዶክመንት) በወራቤ ኮምሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 302 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ለእያንዳንዳቸው በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ተፈላጊ ዕቃዎችን ማቅረብ የሚያስችላቸውን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
- የዚህ ጨረታ ተካፋዮች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ 15000 በባንክ በተመሰከረ C.P.O /የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (በአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30-6:30 30 ሰዓት ከሰዓት ከ7:30-11፡30 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግዥ ፋይናንስና ንብረት ንብረት አስተዳደር ክፍል ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በ15ኛው ቀን በ08፡00 ተዘግቶ በ15ኛ ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የመክፈቻውም ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በህዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0463299263 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
