Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ወላይታ ዞን : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0916599657
  • Website
  • Deadline20 Feb 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Water System Installation

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በልማታዊ ሴፍቲ ኔት ካፒታል በጀት የተለያዩ ግዥዎችን ለመፈፀም ይፈልጋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በልማታዊ ሴፍቲ ኔት ካፒታል በጀት የተለያዩ ግዥዎችን ለመፈፀም የሚፈልግ ሲሆን፤-

በሎት1. የፋብሪካ ውጤቶች፤

በሎት2 የማዕድን ውጤቶች፤

በሎት3 አነስተኛ መስኖ ካናል ግንባታ፣

በሎት4 የውሃ ምንጭ ማጎልበትና ቦኖ ግንባታ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች አሟልተው መቅረብ ያለባቸው መስፈርቶችና ግዴታዎች፤

  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው፤
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Identification Number) ያለው፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት /VAT/ ያለው፤
  4. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  5. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  6. የዘመኑ ታክስ ክሊራንስ /Tax Clearance/ ማቅረብ የሚችል፤
  7. በግንባታ ዘርፍ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የሙያ ምስክር ወረቀት /ብቃት ማረጋገጫ/ ለመስኖ ካናል ግንባታ ደረጃ /WWC/GC-5 እና ከዛ በላይ እንዲሁም የውሃ ምንጭ ማጎልበትና ቦኖ ግንባታ ደረጃ /WWC/GC -6 እና ከዛ በላይ ማቅረብ የሚችል፤
  8. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ/ ብር በመክፈል ከወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ሥራ ሂደት መግዛት ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት Cash Payment Order (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ ብር /20,000/ ሃያ ሺህ ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካልና ፋይናንሻል አንድ ላይ በማድረግ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት የኦርጅናል ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  11. ጨረታው በ31ኛው የሥራ ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  12. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።
  13. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም፤

 

ማሳሰቢያ

* የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፤

* መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር /0916599657/0910274244/0925147581/ ይደውሉ

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender