የአስቱ ቴክኖ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ ለተለያየ ስራ የሚውሉ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል ።
አስቱ ቴክኖ ቢዝነስ ኢንተርኘራይዝ
በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የአስቱ ቴክኖ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ ለተለያየ ስራ የሚውሉ ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሞሉ ተጫራቾች፤
- በተሽከርካሪ አቅራቢነት (ኣስመጪነት ) የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርቲፊኬት (TIN ) ያለው
- በመንግሥት የግብር ሕግ መሠረት ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- አግባብነት ያለው የሙያ ብቃት ሰርተፊኬት ያለው
- በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢነት (አስመጪነት) ሊስት ላይ መመዝገቡን የሚገልፅ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኝ በአስቱ ቴክኖ ቢዝነስ ኢንተርፕራይ የአስተዳደር ሕንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110 በአካል በመገኘት የጨረታ ዶክመንቱን የማይመለስ ብር የምትችሉ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09-29-49-88-83 ደውለው መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
አስቱ ቴክኖ ቢዝነስ ኢንተርኘራይዝ
