Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን
  • Address አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-111-0994
  • Websitehttps://www.ethiotelecom.et
  • Deadline12 Feb 2025, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በባቱና በአሰላ የህንጻ ማሳመር ስራ እና በአዳማና በቢሾፍቱ የጥበቃ ቤት፣ ደርቅ ሽንትቤትና የአጥር ስራ በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/ BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በባቱና በአሰላ የህንጻ ማሳመር ስራ እና በአዳማና በቢሾፍቱ የጥበቃ ቤት፣ ደርቅ ሽንትቤትና የአጥር ስራ በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/ BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል። REQ No: 4271739, 4271740. 4271764. እና 4271765 ቅደም ተከተል።

በዚሁ መሰረት በግንባታ ዘርፍ የተሰማራችሁ፣ ህጋዊ የታደሠ ፍቃድ ያላችሁና ቢያንስ ሁለት አመት የስራ ልምድ ያላቸው በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ደረጃ GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኮንትራከተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

መስፈርት

  1. ጨረታው ከጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
  2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሠ የንግድ ፈቃድ ፣ የተ. እታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
  3. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በግንባታ ዘርፍ የሠሩበትን የስራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 20,000.00/ ሀያ ሺ/ የጨረታ ማስከበሪያ የባንከ ሲ.ፒ.ኦ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሸቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የካቲት 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል::
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘገጅ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቁጥር 022-111-0994 / 022-112-1560 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

ኢትዮ ቴሌኮም

 ደቡብ ምስራቅ ሪጅን

 

Save Tender