የድሬዳዋ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን ለተለያዩ ኤግዚቢሽን፣ ባዛር እና ዝግጅት የሚያገለግል የፕላስቲክ ሸራ ድንኳን ለማሰራት ስለሚፈለግ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ስራውን ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን
ድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ኢ/ክ/ል/ኮርፖሬሽን 01/2017 ዓ.ም
የድሬዳዋ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን ለተለያዩ ኤግዚቢሽን፣ ባዛር እና ዝግጅት የሚያገለግል የፕላስቲክ ሸራ ድንኳን ለማሰራት ስለሚፈለግ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ስራውን ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት -
- በዘርፉ ለ2016 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው፤
- የዘመኑን የግብር ለመክፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /Tin No/ ያለው፤
- የቫት ከፋይነት ሠርተፊኬት ያለው፤
- በአቅራቢነት ዝርዝር ላይ የተመዘገበ ሆኖ የምስክር ወረቀት ያለው፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 15.000.00 (አሥራ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ወይም ካሽ ከመወዳደሪያ ዋጋቸው ጋር አያይዘውና አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ከፍሎ በመውሰድና ዋጋ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታትይ ቀናት ውስጥ በድሬዳዋ አስተዳደር አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን ቢሮ ዲፖ ገበያ ማዕከል 3ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 06 ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በ4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የጨረታው መክፈቻ ቀን በዕረፍት ቀን ወይም በበዓል ቀን ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለጸላቸው እና ውል ከፈጸሙ በኋላ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ /አንድ ወር/ ጊዜ ውስጥ አጠናቀው የመ/ቤቱ ንብረት ክፍል ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፡- 0254 11 1574/ 09-20-89-41-42
በድሬዳዋ አስተዳደር የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን
