Tender Detail

Tender Details

  • Deadline27 Jan 2025, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በጉምሩከ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሀራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የሀራጅ ጨረታ ቁጥር 038/2017

 

በጉምሩከ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሀራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ፡- በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 038/2017 በ17/05/2017 የተለያዩ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ጫማዎች፣ ስፔርፓርት፣ ኮስሞቲክስ እና መዋቢያዎች ፣ የመሬት ምንጣፎች ፣ የተለያዩ የስፖርት መሳሪያዎች ፣ የሞባይል ቀፎዎች፣ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሠጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥሩን ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል፡፡
  2. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው::
  3. በሀራጅ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ድሬዳዋ ጉምሩከ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሪሲት በመውሰድ ዘወትር በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ቀኑ 12፡00 ሰአት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 ሰአት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰአት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል:: ነገር ግን እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር ቅ/ጽ/ ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም::
  4. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ሙድአነኖ የሚገኘው ግቢ ነው::
  5. በሀራጅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት ዕቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት፡፡
  6. በሀራጅ ጨረታ ለወጡት በእያንዳንዱ ዕቃዎች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚሆን ከጨረታ ሰነድ ጋር የሚሸጠውን ለኮዱ የተቀመጠ ብር በባንክ የተረጋገጠ (CPO) በንግድ ባንክ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የሀራጅ ጨረታ ለሚካሄደው በማስታወቂያ መሰረት በእለቱ ጠዋት በ2፡00 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ በ4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ጨረታው ይጀምራል።
  8. በሀራጅ ጨረታ ተጫራቾች ዋጋ ሲሰጡ ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ መሆን አለበት፡፡
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  10. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን ዕቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡
  11. ከላይ በተራ ቁጥር 10 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ  በተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፡፡
  12. የጉምሩክ ኮምሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 025-1-12-49-28 (0911953903) መደወል ይቻላል፡፡

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender