አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት Canon 5D ካሜራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Amhara Road Works Enterprises (ARWE) (የአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት)
በድጋሚ የወጣ Canon 5D ካሜራ ግልጽ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር-አመስድ 12/2017
አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት Canon 5D ካሜራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም :- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡-
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይንም በዘመኑ የተሰጠ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው እና የሞሉት ዋጋ ከ200,000 ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ተጫራቾች በድርጅታችን ስም የተሰራ ማለትም በአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት ወይም AMHARA ROAD WORKS ENTERPRISE በሚል የተዘጋጀ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 36,000 ብር (ሰላሳ ስድስት ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ያለ ቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ዋስትና ከጨረታ ዶክመንቱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ የወጣበትን ቀን ጀምሮ በመቁጠር በ15ኛው ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ በ9:30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ወይም የበዓላት ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 23 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የካሜራው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተያያዘ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ውድድሩ ከቫት ጋር በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ነው፡፡ ስለሆነም ሁሉም ተወዳዳሪዎች የተዘረዘሩትን የካሜራ ክፍሎች ዋጋ መሙላት ይጠበቅባቸዋል። ከተዘረዘሩት የካሜሪ ክፍሎች አንዱን ወይንም ከዚያ በላይ ያልሞላ ተወዳዳሪ ካለ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-320-35-76 መደወል ይችላሉ፡፡
አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት
