Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462128588
  • Website
  • Deadline03 Feb 2025, 2:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Electrical And Electromechanical

የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ ሥራ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ላይ በተዘረዘረው መሰረት በግልጽ ጨረታ አውዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)


 

በድጋሚ  የወጣ  የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር  ሲ/መ/ባ/009/2016

 

የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ ሥራ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ላይ በተዘረዘረው መሰረት በግልጽ ጨረታ አውዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ  መሠረት :-

ተ/ቁ

የዕቃው ዓይነት

1

ኤሌክትሮኒክስ

 

 

 

 

  1. አግባብነት ያለውን በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (tin) ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣ የተጨ.እ.ታክስ (ቫት) ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ የመንግሥት ተቋም በሚያወጧቸው ጨረታዎች ላይ መሳተፍ የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዘር ውስጥ የተመዘገቡ ፣ ሕጋዊ የአቅራቢነት ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በባንክ ገቢ በማድረግ የባንክ ስሊፕ አቅርበው ቢሮ ቁጥር 5 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፋይናንሻል ዋናዉን ሁለት ኮፒ እና ቴክኒካል ዋናውን ሁለት ኮፒዎች ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለኤሌክትሮኒከስ ዕቃ የጠቅላላ ዋጋ 30,000 ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የወጪ ማዘዣ (CPO) ወይም ባንክ ጋራንቲ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (Unconditional bid bond) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሆኖ ከብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ከተሰጠው ባንክ መሆን አለባቸው፡፡
  5. የሚቀርቡ ኤሌትሮኒክስ፣ የስሪት ዘመናቸው እና ሌሎች መጫረቻ ሰነዱ ላይ የተገለጹ መስፈርቶችን የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
  6. ከላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን በታች ያስያዘና እና ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውጪ ይደረጋል።
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዳቸውን የፋይናንሻልና የቴክኒካሉን አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያየ ፖስታ ውስጥ በመክተት በጥንቃቄ በማሸግ ሁለቱንም ለየብቻ አሽገው በአንድ እናት ፖስታ በሰም በማሸግ የድርጅቱን ስምና አድራሻ እና የተወዳደሩበትን ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ዓይነት በግልጽ በመጻፍ እንዲሁም ህጋዊ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ቢሮ ቁጥር 5 ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት 16ኛው ቀን ከ3፡00 እስከ 8፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ዕለት ከቀኑ 9:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ሆኖ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በጨረታ መክፈቻ ቀን በራሱ ምክንያት ሳይገኝ ቢቀር ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉልም።
  9. ተጫራች የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ድርጅት ከጨረታ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  10. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡ ያስያዙትም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረሳል ወደፊትም መ/ቤቱ በሚያወጣው በግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች የሞሉት የመወዳደሪያ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የጨረታው ሂደት ተጠናቅቆ ከአሸናፊው ጋር ውል እስከሚፈረም ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም።
  13. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫትን) ያካተተ መሆኑንና አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የቀረበው ዋጋ ቫት እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልከ ቁጥር 046-212 85 88/046-212-8446 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

መ/ቤቱ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ነው፡፡

 

የሲዳማ  መንገዶች  ባለሥልጣን

ሀዋሳ

 

Save Tender

Supply & Fix Alarm System and Supply of Light Fitting and Distribution Board - Federal Auditor Gener...

READ MORE