Tender Detail

Tender Details

  • Company Lalibela Study Design & Supervision Works PLC (የላሊበላ የጥናት፤ የዲዛይን ቁጥጥር ስራ/ኃላ/የተ/የግል ማህበር)
  • Address ላሊበላ የጥናት፤ ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ባህርዳር ቀበሌ 16 ዶከተር አዛናው ህንፃ ወይም መሪጌታ ጥላሁን የባህል ሕክምና ማዕከል ወይም ባህርዳር አካዳሚ ጀርባ። : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 058 320 024
  • Website
  • Deadline27 Jan 2025, 5:30 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Study And Research And Tools

የላሊበላ የጥናት፤ የዲዛይን ቁጥጥር ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ለ2017 ዓ.ም (እ.ኤ.አ 2025) በጀት ዓመት የተለያዩ መሳሪያዎችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ በማውጣት በግልጽ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Lalibela Study Design & Supervision Works PLC (የላሊበላ የጥናት፤ የዲዛይን ቁጥጥር ስራ/ኃላ/የተ/የግል ማህበር)


 

ግልጽ የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏

 

  1. የላሊበላ የጥናት፤ የዲዛይን ቁጥጥር ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ለ2017 ዓ.ም (እ.ኤ.አ 2025) በጀት ዓመት የተለያዩ መሳሪያዎችን ማለትም፡-

1. የጂኦፊዚክስ መሳሪያዎች፡- 1.1 kaliper (የኬንዚንግ ውፍረት)፤1.2 water quality test kit (የውሃ ጥራት መለኪያ፤ 1.3. PWQT-500 Ground water detector-500m 1.4 GPS INSTRUMENT

2. የአፈር መመርመሪያ መሳሪያዎችን፡- 2.1. HCL (Hydrochloric Acid) 96-98% Acidity, with a glass bottle፤ 2.2 Auger (With Full Extensions)፤ 2.3 Core Sampler፤ 2.4. PH Metter፤ 2.5 Hand Lens (10% magnification power)፤ 2.6. Water Sample Taking Equipment መሳሪያዎችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ በማውጣት በግልጽ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሰነዱን መግዛትና መወዳደር እንድትችሉ ተጋብዛችኋል።

  1. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ያላቸው፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ከሆኑ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትማቅረብ የሚችሉ፤
  4. በስሙ የታተመ ደረሰኝ ያለው፤
  5. ተጫራቾች በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
  6. የዕቃው ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሰነዱ ማግኘት የሚቻል ሲሆን አቅራቢ ድርጅቱ ከላይ የተገለጹትን መስፈርቶችን ማሟላት የሚገባው ሆኖ የጂኦፊዚክስ መሳሪያዎችን እና የአፈር መመርመሪያ መሳሪያዎችን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ያሟላ እና መሙያው ላይ መሥሪያዎችን ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ሞልቶ በሚያቀርበው ዝቅተኛ ዋጋ መሰረት በማድረግ አሸናፊው የሚለይ ይሆናል።
  7. የዋጋ መሙያው ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፣ ስርዝ ድልዝ ካለውም በአቅራቢው በኩል ከተሰረዘው ጎን መፈረም ይገባዋል።
  8. አቅራቢው የነጠላ ዋጋውን በዕቃው ብዛት አባዝቶ ጠቅላላ ዋጋውን ካልሞላ የነጠላ ዋጋው ተይዞ ጠቅላላ ዋጋው ውድቅ ይደረጋል።
  9. ለኩባንያው ጥቅም ሲባል ከነጠላ ዋጋው ይልቅ ጠቅላላ ዋጋው / ጥቅል ዋጋው አዋጭ ሆኖ ካገኘው ጠቅላላ ዋጋውን /ጥቅል ዋጋው መውሰድ ይችላል፤ ወይም ለኩባንያው ጥቅም ሲባል ከጠቅላላ ዋጋው ከጥቅል ዋጋው ይልቅ ነጠላ ዋጋው አዋጭ ሆኖ ካገኘው ነጠላ ዋጋውን መውሰድ ይችላል።
  10. የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በላሊበላ የጥናት፤ ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ገንዘብ ያዥ ሕንፃ 03፤ ቢሮ ቁጥር 003 ማግኘት ይችላሉ።
  11. ተጫራቾች የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ለኩባንያው ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ከሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
  12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሃሳቡን ፋይናንሻልና ቴክኒካል አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ እና ከሁለቱም ፖስታዎች ላይ የኩባንያውን ሙሉ አድራሻ ከስልክ ቁጥሩ ጋር እንዲሁም የተወዳዳሪው ሙሉ አድራሻ ከስልክ ቁጥሩ ጋር በመጻፍና የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ በላሊበላ የጥናት ፣ ዲዛይን እና ቁጥጥር ሥራ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ውስጥ ለዚሁ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት‍‍‌‍‍‍‌‍‍‍‍‌‍‌‍ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምር በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ መቅረብ አለበት።
  13. ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም በራሳቸው ጊዜ ባይገኙም በላሊበላ የጥናት፤ ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ህንፃ ቁጥር 01፣ ቢሮ ቁጥር 001 በ10ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ይታሸግና በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል። የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ወደሚቀጥለው የሥራ መጀመሪያ ቀን በማዛወር ከላይ በተገለጸው ተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  14. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ስለጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ዝርዝር መረጃ ከፈለጋችሁ በላሊበላ የጥናት፣ ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራኃላ/ የተ/የግ/ማህበር ህንፃ ቁ 01፣ ቢሮ ቁጥር 001 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 0241/058 320 1366 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

የኩባንያው አድራሻ ፡- ላሊበላ የጥናት፤ ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ባህርዳር ቀበሌ 16 ዶከተር አዛናው ህንፃ ወይም መሪጌታ ጥላሁን የባህል ሕክምና ማዕከል ወይም ባህርዳር አካዳሚ ጀርባ።

 

ስልክ ቁጥር ፡- 058 320 024/058 320 1366 ፋክስ ቁጥር 058-320-43-39 ባህርዳር /ኢትዮጵያ/

 

የላሊበላ የጥናት፤ የዲዛይን ቁጥጥር ስራ/ኃላ/የተ/የግል ማህበር

 

Save Tender