የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩ የተለያዩ እቃዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ቁጥር ጣበስፋ/አግ/ብግጨ/04/2017
የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩ የተለያዩ እቃዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በሎት-1 Johndeer 941OR Tractor መለዋወጫ
በሎት-2 Versatile Tractor መለዋወጫ ሞዴል 2375
በሎት-3 Agrotroon Iractor መስዋወጫ ሞዴል BF6M1013FC
በሎት-4 YTO Tractor መለዋወጫ ሞዴል 1004
በሎት-5 YTO Tractor መለዋወጫ ሞዴል 1304
በሎት-6 YTO Tractor መስዋወጫ ሞዱል 1804 እና
በሎት 7 የመስኖ መለዋወጫ ዕቃዎች (Dragne Sprinkler) በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ የ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተስጠ የታክስ ክሊራንስና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ አግባብነት ያለው አካል ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000577307637 በመክፈልና የባንከ አድቫይስ በማቅረብ በተራ ቁ. 4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታው ማስረከቢያና መከፈቻ አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው።
አዲስ አበባ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ፣ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንጻ።
ብሎክ A ቢሮ ቁጥር B008
ስልክ ቁጥር 011 558 6725/09 12 031 748፣ አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ የጠቅላላ ዋጋውን 2% ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው።
- የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ነው። ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር - 0115 58-67-25 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ
