Tender Detail

Tender Details

  • Company የሮቤ ከተማ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ልማት ጽ/ቤት
  • Address ሮቤ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022 865 0893
  • Website
  • Deadline02 Feb 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የሮቤ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማው ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን ነገሮች በግልፅ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሮቤ ከተማ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ልማት ጽ/ቤት


 

የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏

 

የሮቤ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማው ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ

  • የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ቋሚና አላቂ ዕቃዎች፣
  • የፅዳት ዕቃዎች፣
  • የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣
  • ፈርኒቸሮች፤
  • የሕንጻ መሣሪያዎችን፣
  • የተለያዩ ህትመቶች፣
  • ሞተር ሳይክሎች፣
  • የከባድና ቀላል መኪና ጎማዎችንና መለዋወጫ፣ የከባድ መኪና ቀላል መኪና ጥገናዎች፣
  • የተለያዩ ምግቦች እና መጠጦች ከነመስተንግዶ፣
  • የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎች፣
  • የሠራተኞች ደምብ ልብስ የሚሆኑ የተለያዩ ብትንና የተዘጋጁ ልብሶች እንዲሁም ጫማዎችን በግልፅ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲወዳደሩ እንጋብዛለን፡-

  1. ተጫራቾች በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ለመካፈል የሚያስችል በሚወዳደሩበት ዘርፍ የተሰማሩበት ተጓዳኝ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፍለው ያሳደሱና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት)፣ ቲን ነምበር፣ ቲኦቲ ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ 80,000 (ሰማኒያ ሺህ) ብር የያዘ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ መስፈርት መሠረት እውቅና የተሰጣቸውን ዕቃዎች የሚያቀርብ፡፡
  5. ተጫራቾች ለሁሉም እቃዎች ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታዎች በሰም አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. አቅራቢው ድርጅት ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ከ5ኛው ቀን በኋላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ በመ/ቤቱ ቀርቦ ውል መፈራረም ይኖርበታል፡፡
  7. አቅራቢው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ማንኛውንም ወጪ በመቻል መ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ሮቤ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን በመከፈል ሰነዱን ከገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው በማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት‍‍‌‍‍‍‌‍‍‍‍‌‍‌‍ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ይከፈታል፡፡
  10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 022 865 0893/09 12 251 615 ደውለው ይጠይቁ፡፡

 

የሮቤ ከተማ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ልማት ጽ/ቤት

 

Save Tender