በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ስር የሚገኘው የሚሊንየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2017 ዓ.ም ለትምህርት ቤቱ በሚያስፈልገውን ቋሚ እቃ እና ኤሌክትሮኒክስ እንዲሁም የደንብ ልብሶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትይፈልጋል፡፡
ሚሊንየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 02/2017
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ስር የሚገኘው የሚሊንየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2017 ዓ.ም ለትምህርት ቤቱ በሚያስፈልገውን ቋሚ እቃ እና ኤሌክትሮኒክስ እንዲሁም የደንብ ልብሶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ፡-
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለሚጫረቱበት አይነት(ሎት) የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሀምሳ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት በ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘው የሚሊኒየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናስ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- በዚሁ መሰረት ለሎት1 የደንብ ልብስ ብር 5000፣ ለሎት 2 ቋሚ እቃ እና ኤሌክትሮኒክስ ብር 5000 በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡
- የሚቀርቡት ነጠላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ያካተተ እና የቀረበው ነጠላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ጨምሮ መሆኑን መግለጫ መስጠት አለበት፡፡
- ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ካደራጃቸው አካል በጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ የምታፅፉ ጥቃቅን እና አነስተኛ አቅራቢዎች የተሰማራችሁበትን የንግድ ስራ መስክ/ዘርፍ/ የሚገልፅ ደብዳቤ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በሚገባ በታሸገ እና ማህተም ባረፈበት ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰአት ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመቅረብ የሚወዳደሩበት ዋጋ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ናሙና ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዋጋ 10 ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች በሙሉ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ወይም በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ወዲያው 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- የካ ክ/ከተማ ወደ ኮተቤ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ 02 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ህዝብ ደህንነት በሚያስወጣው አስፋልት ከፍ ብሎ ወረዳ 10 አጠገብ ሚሊኒየም አጠቃላይ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት፡፡ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ 011 668 34 63 ወይም ወረዳ 10 ሚሊኒየም አጠቃላይ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናስ ቢሮ በግንባር በመቅረብ አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ሚሊንየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
