የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 61 እና 62 በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ እቃዎችን ምግብ ነክ፣ ጫማዎች፣ የንጽህና መጠበቂያ እቃዎች፣ ኮስሞቲክሶች፣ ቁሳቁች፣ አልባሳቶች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
ለመጀመሪያ ዙር የወጣ የግልጽ ጨረታ
ማስታወቂያ ቁጥር (007/2017)
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 61 እና 62 በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ እቃዎችን ምግብ ነክ፣ ጫማዎች፣ የንጽህና መጠበቂያ እቃዎች፣ ኮስሞቲክሶች፣ ቁሳቁች፣ አልባሳቶች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በተገለፀው የጨረታ መስፈርት መሰረት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ስርተፊኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ እና ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ለሚያወጡ እቃዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30-6፡00 እና ከሠዓት በኋላ 7፡30-11፡00 ሰዓት ቅዳሜ ጠዋት 2፡30-6፡00 ድረስ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል በጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ዋስትና (CPO) በጉምሩከ ኮሚሽን አሶሳ ቅ/ጽ/ቤት ስም በባንክ በተረጋገጠ አሠርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከ9/5/2017 እስከ 15/5/2017 ከጠዋቱ 3፡45 ድረስ አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመምጣት እቃዎቹን ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ጨረታው በቀን 16/5/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከረፋዱ 4፡00 ላይ የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታው መክፈቻ ቦታ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያሲያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ተጫራቾች ደግሞ በ3 የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ05 ቀናት ውስጥያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ ክፍያ ከፈፀመ በ5 ቀናት ውስጥ እቃዎቹን ተረክበው ማንሳት ይኖርባቸዋል።
- ከላይ በተራ ቁጥር 7 እና 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና እቃዎቹን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት (CPO) ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ እቃዎቹ በድጋሜ ለጨረታ ይቀርባሉ።
- ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- 057-44-83-74 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት
