በደ/ኢት/ያ ክልል መ/የወላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዘመን በሴፍቲኔት ካፒታል በጀት ለድህነት ቅነሳ ሴክተር መ/ቤቶች ለአገልግሎት የሚሆኑ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
በደ/ኢት/ያ ክልል መ/የወላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ኢት/ያ ክልል መ/የወላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዘመን በሴፍቲኔት ካፒታል በጀት ለድህነት ቅነሳ ሴክተር መ/ቤቶች ለአገልግሎት የሚሆን
በ Lot- 1 ለንብ ማነብ ሥራ እና ለማር ማጣሪያ የሚያስፈልጉ ጠቅላላ ቁሳቁስ ግዥ፣
በ Lot-2 ለችገኝ ጣቢያ ሼዲ /Net-house/ ግንባታ ሥራ የሚያስፈልግ ሙሉ ዕቃ ግዥ፤
በ Lot 3 ለውሃ ዝርጋታና ግንባታ የሚያስፈልጉ የተለያዩ የውሃ ዕቃ ግዥ ፤
በ Lot- 4 ትልቁ የውሃ ጀኔሬተር ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡-
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች፡-
- በተጠቀሱ ዕቃዎች በየዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ወይም E-Gp online registered የተደረገ፤
- ከሚመለከተው ክፍል የተሰጠ የታክስ ክሊራንስ ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፤
- በመንግሥት ግዥ ለመሳተፍ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 30 ተከታታይ የሥራ ቀን ድረስ ለዚህ የተዘጋጀውን ዝርዝር ስፔስፊኬሽን የያዘውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በየሎት በመክፈል ከዳ/ጋ/ወ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 ሠነድ በመውሰድ የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ እና ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናሉን በአንድ ላይ በማሸግ የኦርጅናል ሁለት ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ የድርጅቱ ስም፤ ፊርማ እና ማህተም ተደርጎ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን መጨመር ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ31ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 08:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ/ በየሎት በጥሬ ገንዘብ ወይም በCPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑ መገለጽ አለበት ካልተገለጸ የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ እንደሆነ ተቆጥሮ ውድድሩ ይካሄዳል፡፡
- አሸናፊ አቅራቢ የሚለየው በጠቅላላ ዕቃ ያቀረበው ዝቅተኛ ዋጋ መሠረት ይሆናል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች የጨረታ ውል ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ 10% ከታወቀ ባንክ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ክፍያ የሚፈጸመው አሸናፊው ተጫራች ያሸነፋቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ መጋዘናችን ሲያቀርብ እና የጥራት ደረጃቸው በጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴ ወይም በባለሙያ ሲረጋገጥ ብቻ ነው ::
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-559-01-14 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በደ/ኢት/ያ ክልል መ/የወላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት
