Tender Detail

Tender Details

  • Company በቤንች ሸኮ ዞን የጉራፈርዳ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
  • Address ቤንች ሸኮ ዞን : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 17 77 16 04
  • Website
  • Deadline31 Jan 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Water Construction Machinery And Equipment

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቤንች ሸኮ ዞን የጉራፈርዳ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለጉራፈርዳ ወረዳ ኩጃ ማዘጋጃ ቤት የተለያዩ የውሃ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በቤንች ሸኮ ዞን የጉራፈርዳ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት


 

ግልጽ  የጨረታ  ማስታወቂያ

 

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቤንች ሸኮ ዞን የጉራፈርዳ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለጉራፈርዳ ወረዳ ኩጃ ማዘጋጃ ቤት የተለያዩ የውሃ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ፡-

በጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው::

  1. በውሃ እቃዎች አቅራቢነት በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡-
  2. በውሃ እቃዎች አቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ certified payment(CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የባንክ ዋስትና ከሆነ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና / Unconditional Bank Guarantee/ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በግዥ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመከፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች መ/ቤቱ በሚያቀርበው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት ተፈርሞበት ፋይናንሻል እና የቴከኒካል ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያ ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት በጉራፈርዳ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 02 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. ጨረታው ማስታወቂያው በወጣ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት የሚከፈት ሆኖ ጨረታው የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ሆኖ ተጫራቾች በሰዓቱ ባይቀርቡም የጨረታው ሂደት አይስተጓጎልም፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 0918511968 0919331542 እና 0913324728 መጠየቅ ይቻላል።

 

የጉራፈርዳ  ወረዳ  ፋይናንስና  ኢኮኖሚ  ልማት  ጽ/ቤት

 

Save Tender