የሆሳዕና ከተማ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሠረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች (ለመኖሪያ እና ለንግድ) የተዘጋጀ ቦታን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቶች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
የሆሳዕና ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገ/ቶች ጽ/ቤት
የሊዝ ቦታ ጨረታ ማስታወቂያ
- የጨረታው ዙር:- 1ኛ
- የጨረታ ዓይነት: መደበኛ
- የሆሳዕና ከተማ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሠረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች (ለመኖሪያ እና ለንግድ) የተዘጋጀ ቦታን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቶች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለንግድ 500 ብር /አምስት መቶ ብር/ ለመኖሪያ 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከማዘጋጀ ቤቱ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 3 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ መግዛት የሚቻል መሆኑን እናስታውቃለን። ለመደበኛ ጨረታ በ10ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው እስከ 9፡00 ሰዓት ብቻ ነው::
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል፡፡
- የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ቦታውን መጎብኝት ለሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሀ-ግብር መሠረት የሚናስጎበኝ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት በሆሳዕና ከተማ አቢዮ ኤርሳሞ ስታዲየም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡ 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ማዘጋጀ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ዌብ ሳይት www.hosannaca.gov.et ማግኘት ይቻላል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡
046-555-36-45
046-555-23-55
046-555-23-10
የሆሳዕና ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገ/ቶች ጽ/ቤት
ሆሳዕና
