Tender Detail

Tender Details

  • Company የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት (Defence Construction Design Enterprise)
  • Address ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን የነበረበት የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ ግራውንድ ላይ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 896 06 33
  • Websitehttps://dcde.gov.et/#
  • Deadline30 Jan 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Security Service

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ የጥበቃ እና ፋተሻ አገልግሎት የሚሰጡ ሰራተኞችን ከኤጀንሲዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል::

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት (Defence Construction Design Enterprise)


የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

መከላከያ ሚኒስቴር

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት

The Federal Democratic Republic of Ethiopia

Ministry of Defense

Defense Construction Design Enterprise

 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCDE 019/2017

 

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ የጥበቃ እና ፋተሻ አገልግሎት የሚሰጡ ሰራተኞችን ከኤጀንሲዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል::

በዚህም መሰረት ፡-

  1. ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የገበሩበትን ንግድ ፈቃድ ተ.እ.ታ (VAT) ወይም የሽያጭ ታክስ (Turn over Tax) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው በደንቡ መሠረት ከመንግስት የግዥ ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡ፣ በማንኛውም ጨረታ ለመሳተፍ የሚችል Tax Clearance እና ሌሎች ማስረጃዎች ማቅረብ አለባቸው:: በተጨማሪም በማንኛውም የመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ የታገዱ ድርጅቶች ዲዛይን ድርጅቱ መረጃውን ካገኘ በጨረታ እንዳይሳተፉ ወይም ከጨረታ ውጪ እንዲሆኑ ይደረጋል::
  2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30- 6፡30 ከሰዓት ከ7፡30-11:30 እስከ በድርጅታችን ፋይናንስ ዴስክ መውሰድ ይችላሉ::
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ በሶስት ኤንቬሎፕ ሆኖ

1ኛ. አንደኛው ኢንቬሎፕ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻው በፖስታ በማሸግ ፋይናሽያል ፕሮፖዛል በማለት የፋይናሽያል ፕሮፖዛል የሚቀርብ ይሆናል::

2ኛ. ሁለተኛው ኢንቬሎፕ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻው በፖስታ በማሸግ ቴክኒካል ፕሮፖዛል በማለት ቴክኒካል ፕሮፖዛል የያዘ እና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)፣ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ እና የግብር መለያ ቁጥር (TIN) ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ወዘተ የያዘ መሆን አለበት።

3ኛ የጨረታ ማስከበሪያ በድርጅታችን ትክክለኛ ስም የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት (Defense Construction Design Enterprise) ስም የተዘጋጀና ለየብቻዉ በማሸግ የሚቀርብ ይሆናል:: በዚህ ዓይነት ተለያይቶ ያልቀረበ ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም ለተጫራቹ ይመለስለታል::

  1. የጨረታ ማስከበሪያ እንደ ተጫራቹ ምርጫ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  2. ድርጅታችን ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
  3. ጨረታው ከጥር 07/2017 እስከ ከጥር 22/2017 ዓ.ም አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በቀን ከጥር 22/2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥኑ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ይካሄዳል::
  4. የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይዛወራል::
  5. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱ በድርጅታችን ፋይናንስ ዴስክ መውሰድ ይጠበቅባችኋል::

 

አድራሻ ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 896 06 33/ 011 896 06 23

አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር

ኮርፖሬሽን የነበረበት የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ ግራውንድ ላይ

 

Save Tender