በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በስልጤ ዞን ላንፍሮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለጤና ጽ/ቤት እና ለት) ጽ/ቤት በዋን ዋሽ ፕሮግራም በ2017 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው ለወንቴ ሎላ ጤና ጣቢያ እና ለመ/ጋገቦ ት/ቤት ለሚያሠራቸው ግንባታዎች በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በስልጤ ዞን ላንፍሮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በስልጤ ዞን ላንፍሮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለጤና ጽ/ቤት እና ለት) ጽ/ቤት በዋን ዋሽ ፕሮግራም በ2017 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው ለወንቴ ሎላ ጤና ጣቢያ እና ለመ/ጋገቦ ት/ቤት ለሚያሠራቸው ግንባታዎች በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ደረጃቸው G.C/B.C 9 እና ከዛ በላይ የሆነ ፡-
ሎት 1 እንስሌተር /incinilator/ የእንግዴ ልጅ መቅበሪያ /Placenta pit/፣ የአመድ መቅበሪያ ግንባታ ለወንቴ ሎላ ጤና ጣቢያ
ሎት 2 መፀዳጃ ቤት ግንባታ ለወንቴ ሎላ ጤና ጣቢያ
ሎት 3 የወንዶች መፀዳጃ ቤት ግንባታ ለመ/ጋገቦ ት/ቤት
ሎት 4 የሴቶች የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ከፍል (MHM) – ግንባታ መጋገቦ ት/ቤት
በዚህም መሠረት ተጫራቾች
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ፣
- የታደሰ የንግድ ፈቃድና የሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የዘመኑን የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ፤
- የጨረታ ዋስትና ለሎት 1 – 8,000 /ስምንት ሺህ ብር/፣ ለሎት 2፡10,000 /አስር ሺህ ብር/ ፣ለሎት 3 -10,000 አስር ሺህ ብር እና ለሎት 4፡- 15000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ለየብቻ በካሽ ወይም በCPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የድርጅቱን አወቃቀር እና ከዚህ በፊት የሠሯቸውን ሥራዎች የሚገልጽ የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ሰነዱን ላንፍሮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 09 በመቅረብ ለሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን፤ የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሺያል ዶከመንቱን በሚገባ በመሙላት ስርዝ ድልዝ በሌለው ጽሑፍ አንድ ኦርጅናል እና 2 ኮፒ ለየብቻ ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦርጅናል እና 2 ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የሥራ ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ላንፍሮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ዕለት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ሂደት ላይ የማጭበርበር ድርጊት ለመሥራት የሞከረ እንደሆነ ከጨረታው ውጪ ይደረጋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ቢያሸንፍ ከታወቀ የፋይናንስ ተቋም በሁኔታዎች ያልተገደበ -የብድር አገልግሎት ማግኘት እንደሚችል ደብዳቤ ማቅረብ አለበት፡፡
ማሳሰቢያ ፡-
- ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ
- የተወዳዳሪ ተቋራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መከፈቻ ቀኑን አይለውጠውም
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር :- 09 77 94 68 26/09 13 17 02 12/ 09 33 43 49 98/ 09 26 94 49 00 ደውሉ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በስልጤ ዞን ላንፍሮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
