የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ የተወረሱ የመገናኛ መሣሪያ አልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ፣ የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች፣ የሞተር ሳይክል እና መኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ምግብ ነክ እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች በግልጽ እና በሐራጅ በጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 27/2017
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ የተወረሱ የመገናኛ መሣሪያ አልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ፣ የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች፣ የሞተር ሳይክል እና መኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ምግብ ነክ እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች በግልጽ እና በሐራጅ በጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- የግልፅ ተሳታፊ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ሲሆን ግምታዊ ዋጋ ከብር 500 ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያ ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ፣ ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የግልጽ ጨረታ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO፣ የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ በምግብ ነከ እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች የሐራጅ ጨረታ ለሚሳተፉ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ኮድ ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው /በስድስተኛው/ ቀን ጠዋት ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡05 የሚከፈት ሲሆን የሐራጅ ጨረታ ግልጽ ጨረታው እንዳለቀ ከ10 ደቂቃ በኋላ በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ይጀመራል፣ ነገር ግን ጨረታው በበዓል እሁድ ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ ከነቫቱ በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ወይም ፖስታ ማቅረብ አለባቸው:: ከዚህ ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ ቤቱ ለመቀበል አይገደድም::
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋ እና መግለጫ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም ::
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በሶስት (03) የሥራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ በሚሰጡት ዋጋ ምክንያት የሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ነው፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር ፡- 0462125396
በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ቅ/ጽ/ቤት
