Tender Detail

Tender Details

  • Deadline22 Jan 2025, 10:45 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Materials

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 እና በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/211 መሰረት የተተዉ ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን በእቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 መሠረት የተተዉ ንብረቶችን እና እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የተተዉ  ዕቃዎች  ግልፅ  የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏

የግልጽ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ቁጥር  ግ-40/2017 ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 እና በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/211 መሰረት የተተዉ ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን በእቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 መሠረት የተተዉ ንብረቶችን ማለትም

  • SHOE OUTSOLE AND MOULD, የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የግንባታ ዕቃ፣ COFFEE GRINDER፣
  • የተለያዩ ኔትዎርክ እቃዎች፤ V-BELT STSR COLOR PRINTING PAPER,
  • INTLEGENCE COLD SORTER MACHINE AND OTHERS, CYLINDER FILLED WITH UN1058 LIQUEFIED GASSNON FLASMMABLE CHALGEDWITH NITROGEN CARBONDIOXIDEOR AIR & PIGMENT BASED ON TITANIUM DIOXIDE AND OTHERS እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሠነድ እና መመሪያ መግለጫ እንዲሁም የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት‍‍‌‍‍‍‌‍‍‍‍‌‍‌‍ በኋላ ከቀኑ 7:00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡ 30 እስከ ቀኑ 10፡30 አንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5:30 የማይመለስ ብር 100 (እንድ መቶ) በመክፈል ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ እና ከዋናው መስሪያ ቤት ገቢ ሂሳቦች ቡድን ሰነድ በመግዛት መመልከት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣ ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ስም ETHIOPAN CUSTOMS COMMISSION MOD]O BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፣ አዳማ አና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት፡፡ ተሳታፊዎች ዋጋ መሙላት የሚችሉት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተዘጋጅቶ ማህተም ያረፈበት ሰነድ ላይ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አሰቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን ዕቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡ በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ተሽጦ የተወሰደ እቃ ተመላሽ አይደረግም፤ ለእቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም፡፡
  5. የግልፅ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ተሳታፊ ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃዎች ለመግዛት የሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ፤ የሞሉበት ሠነድ በተራ ቁጥር 2 የተገለፁትን ማስረጃዎች ኮፒ እና ያቀረቡት የመጫረቻ ዋጋ 5% ለጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት እስከ መጨረሻው ቀን ጠዋት 4፡45 ድረስ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሳጥን ማስገባት ይቻላል፡፡ የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሣጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
  6. የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበት ቀን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡45 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  7. ማንኛውም በግልጽ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፣ በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሽያጭ ውድድር ላይ የዕቃ አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ውድድር ማግለል አይቻልም እና የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  8. የግልጽ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ው አሸናፊ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት፡፡ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
  9. በተራ ቁጥር 8 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳ/ ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል፡፡ ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሽያጭ ይወገዳል፡፡
  10. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል፡፡
  11. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ የአቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው፡፡ በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ተሽጦ በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ አሸናፊው የተወሰደ እቃ አይመለስም፡፡
  12. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር፡- 022-236-90 94 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በገቢዎች  ሚኒስቴር  ጉምሩክ  ኮሚሽን  የሞጆ  ጉምሩክ  ቅርንጫፍ  ጽ/ቤት

 

Save Tender