በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡታጅራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለ2017 በጀት ዓመት ለሚገነባው የተለያዩ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ኮንክሪት ሚክሰር እና ቫይብሬተር እና የአርማታ ብረት በሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የቡታጅራ ውሃ ሥራዎች ድርጅት
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡታጅራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለ2017 በጀት ዓመት ለሚገነባው የተለያዩ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ፤
ሎት-1. ኮንክሪት ሚክሰር እና ቫይብሬተር
ሎት-2. የአርማታ ብረት በሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለበት፤
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ በፋይናንስ ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይ ለመሆናቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃዎችን ከዋናው ጋር የተገናዘበ በፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የዕቃዎቹም የጨረታ ሰነድ ማስታወቁያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ቡታጅራ ከተማ ውሃ አቅርቦትና ፍሣሽ አገልግሎት ድርጅት ግቢ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ የሚቻል ሲሆን አድራሻችንም ከቡታጅራ ንግድ ባንክ በስተጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ ሴራና አዳራሽ ጀርባ ይገኛል፡፡
- የሚጫረቱባቸውን ዕቃዎች በመለየት በዓይነታቸው እና በመጠናቸው የሚሸጡባቸውን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የሚጫረቱባቸውን ዘርፍና የተጫራቹን ስም በግልፅ በመፃፍ የድርጅቱ ማህተም አርፎበት በአስራ ስድስተኛው ቀን ሰነዱን በገዙበት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በዚሁ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና 2 ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ ከቀኑ 8፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች/ወኪሎቻቸው ባይኖሩም መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ከመክፈት አይታገድም::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሁሉም የተዘረዘሩት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ብቻ ከጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ የተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት እቃዎችን ቡታጅራ ከተማ ድረስ የሚያቀርብ መሆኑን እያሳወቅን መ/ቤቱ በወሰነለት ቀን ካላቀረበ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስም::
- ማንኛውም ተጫራች ሌላው ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም::
- አሸናፊ ድርጅቶች ማሸነፋቸው እንደተገለፀላቸው ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል መግባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ በሁለት ቀናት ውስጥ የሚያስረክብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ሊገኙ ባይችሉ መ/ቤቱ ጨረታውን ከፍቶ የሚያወዳድር መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች ፡-
Fax:-046 115 1792/ Mobile 0910 966 823/ 0912 475 709
የቡታጅራ ውሃ ሥራዎች ድርጅት
