በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በዋን ዋሽ ፕሮጀክት በጀት በባጥና የከራስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሴት ተማሪዎች መጸዳጃ ቤት ግንባታ እና በተክለሃይማኖት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሴት ተማሪዎች ንጽህና መጠበቂያ ቤት ግንባታ እንዲሁም የምሁርና አክሊል ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በግናብ ጤና ኬላ ቅጥር ግቢ ውስጥ የመጸዳጃ ቤት ግንባታ በሐዋሪያት ከተማ የማምረቻና የመሸጫ ሼድ ግንባታ፤ በሃዋሪት ጤና ጣቢያ ቅጥር ግቢ ውስጥ የውሃ መስመር ስራ እና የአመድ ማስወገጃ ግንባታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋሉ፡፡
በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- 0001
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በዋን ዋሽ ፕሮጀክት በጀት በባጥና የከራስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሴት ተማሪዎች መጸዳጃ ቤት ግንባታ እና በተክለሃይማኖት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሴት ተማሪዎች ንጽህና መጠበቂያ ቤት ግንባታ እንዲሁም የምሁርና አክሊል ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በግናብ ጤና ኬላ ቅጥር ግቢ ውስጥ የመጸዳጃ ቤት ግንባታ በሐዋሪያት ከተማ የማምረቻና የመሸጫ ሼድ ግንባታ፤ በሃዋሪት ጤና ጣቢያ ቅጥር ግቢ ውስጥ የውሃ መስመር ስራ እና የአመድ ማስወገጃ ግንባታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋሉ፡፡
በመሆኑም፡-
- GC/BC ደረጃ 9ና ከዚያ በላይ የታደሰ የግንባታ ፈቃድ ያላችሁ፤
- የንግድ ምዝገባ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለምሁርና አክሊል ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት ግዢ ቢሮ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት እስከ ከረፋ 5፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ። አንድ ተጫራች መውሰድ የሚችለው ሁለት ሰነድ ብቻ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ዶክመንት ሲያቀርቡ፡-
- ሀ. ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ቅጂ ሰነዶችን እያንዳንዳቸው በታሸገ ፖስታ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ በምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከኦሪጅናል ዶክመንት ጋር በማድረግ እና ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ ቴክኒካል በሚል በመለየት፤
- ለ. ፋይናንሽያል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ቅጂ ሰነዶችን እያንዳንዳቸው በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ ፋይናንሺያል በሚል በመለየት እስከ 21ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ አላማ በተዘጋጀው የመጫረቻ ሰነድ ማቆያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። በ8፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ይታሸጋል።
- የጨረታው ቴክኒካል ዶክመንት በሃያ አንደኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታው እንዳይከፈት አያደርግም።
- የፋይናንሺያል (የፕሮጀክቱ የግንባታ ዋጋ) ከቴክኒካል ግምገማ ውጤት በኋላ የቴከኒክ ግምገማውን ያለፉ ተጫራቾች ሰነድ ብቻ ጽ/ቤቱ በማስታወቂያ በሚገልጸው ቀን ይከፈታል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይተላለፋል።
- አጠቃላይ የቅሬታ አቀራረብና አፈታት በተመለከተ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት እንደገና ተሻሽሎ በወጣው ግዢ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 28/2010 መሰረት ይሆናል።
- ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ፡- 011-3-43-01-73/ 011-3-43-06-14 ይደውሉ።
በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
