የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ ተሸከርካሪዎች/መኪናዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል::
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት (Defence Construction Design Enterprise)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCDE 018/2017
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ ተሸከርካሪዎች/መኪናዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል::
በዚህም መሰረት፡-
- ማንኛውም ተጫራች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የውጪ አገር ተጫራቾች በሚሆኑበት ጊዜ በተቋቋሙበት አገር የተሰጣቸውን የኩባንያ ምዝገባ ወረቀት ወይም ፈቃድ ወዘተ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ስነዱ በድርጅታችን ፋይናንስ ዴስክ መውሰድ ይጠበቅባችኋል::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በTOR በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ከተገለፀው ቀንና ሰዓት በፊት በድርጅቱ የግዥ ዴስክ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ ፣ እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል::
- የጨረታ ማስከበሪያ እንደ ተጫራቹ ምርጫ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ከጥር 04 ቀን 2017 ዓ/ም እስከ ጥር 19 ቀን 2017 ዓ/ም አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጭን ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥ ዴስክ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ይካሄዳል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም::
አድራሻ ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 896 06 33/011 896 06 23
አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን
የነበረበት የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ ግራውንድ ላይ
