ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን Galvanized pipe 6' and Flange 6" በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
የጨረታ ማስታወቂያ
ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን Galvanized pipe 6' and Flange 6" በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
|
ተ/ቁ |
የእቃው አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
ዋጋ ከቫት በፊት |
|
1 |
Galvanized pipe 6” or (152.4mm) |
በቁጥር |
180 |
|
|
2 |
Flange 6” or (152.4mm) |
በቁጥር |
360 |
|
በመሆኑም ተጫራቾች
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ::
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጸውን እቃ የአንዱን ዋጋ ከቫት በፊት በመሙላት በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ሳር ቤት ግደይ ገ/ህይወት ህንጻ 3ኛ ፎቅ አ.አ. ስልክ፡ 251114-42-19-28/0930-30-41-10 ግዢ ክፍል እና ድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ስልክ ቁጥር 0935-98-50-83/0946-43-93-94 ግዢ ክፍል ማስገባት ይችላሉ::
- ጨረታው ጥር 15/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ ጥር 19/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ በሚገኘው ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ከጠዋቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 3 ወራት ህጋዊ ሆኖ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. 100,000.00 (መቶ ሺህ) ብር ማስያዝ አለባቸው::
- ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 7 የስራ ቀናት ውስጥ ለገዢው እቃዎቹን ማስረከብ ይጠበቅበታል::
ማሳሰቢያ ፡-
- ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል:: መ/ቤቱም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
