Tender Detail

Tender Details

  • Company በአራዳ ክ/ከተማ የአዋሬ ጤና ጣቢያ
  • Address በቀድሞ ስሙ የካ ክ/ከተማ አቧሬ ጤና ጣቢያ ተብሎ የሚጠራው በአሁኑ በአራዳ ከ/ከተማ እዋሬ ጤና ጣቢያ ንጋት ኮከብ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ፊት ለፊት 4ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 404 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118688278
  • Website
  • Deadline22 Jan 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Pharmaceutical Products

በአራዳ ክ/ከተማ አዋሬ ጤና ጣቢያ የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ መድኃኒቶች እና ለፅዳት አገልግሎት የሚውል የፕላስቲከ ጓንት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአራዳ ክ/ከተማ የአዋሬ ጤና ጣቢያ


 

የጨረታ  ማስታወቂያ

 

በአራዳ ክ/ከተማ አዋሬ ጤና ጣቢያ የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ መድኃኒቶች እና ለፅዳት አገልግሎት የሚውል የፕላስቲከ ጓንት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡

    1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
    2. በመንግስት ግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ያላቸው፡፡
    3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
    4. ከላይ የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ከአራዳ ክ/ከተማ አዋሬ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ላይ የግዥ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 404 ቀርበው 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው ሰነዱን በመውሰድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሰራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን የአንዱን ዋጋ ቫትን ያካተተ በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል፡፡
    5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግል የሚጫረቱበት ዋጋ ለተለያዩ መድኃኒቶች /8,000.00/ ስምንት ሺህ ብር / ለፅዳት አገልግሎት የሚውል የፕላስቲከ ጓንት 2,000.00  /ሁለት ሺህ ብር ብቻ/ ለአራዳ ክፍለ ከተማ አዋሬ ጤና ጣቢያ ስም ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ በሲፒኦ /C.O/ በታሸገ ኢንሸሎፕ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
    6. ተጫራቾች ለጨረታው የገዙበትን ኦሪጂናል ሰነድና ኮፒውን በሁለት ፓስታ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
    7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ናሙና /ሳምፕል/ ማቅረብ እና መድኃኒቶች የአገልግሎት ዘመናቸው አንድ ዓመት እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
    8. ተጫራቾች ከገዙበት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልተው የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
    9. ጨረታውም ማስታወቂያው ከወጣበት በአስራ አንደኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በእለቱ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአራዳ ክ/ከተማ አዋሬ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 408 በግልጽ ይከፈታል፡፡
    10. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ ፡-

በቀድሞ ስሙ የካ ክ/ከተማ አቧሬ ጤና ጣቢያ ተብሎ የሚጠራው በአሁኑ በአራዳ ከ/ከተማ እዋሬ ጤና ጣቢያ ንጋት ኮከብ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ፊት ለፊት 4ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 404

  • ለተጨማሪ ማብራሪያ
  • በስልክ ቁጥር 0118688278 ደውሉው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በአራዳ ክ/ከተማ የአዋሬ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender