Tender Detail

Tender Details

  • Deadline28 Jan 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Billboards And Digital Advertising

ተቋማችን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቢሮ ስም እና አድራሻ (ታፔላ) ሥራ አቅርቦትና ገጠማ እና Fire Extingusher & Installation Service በግልጽ ጨረታ አወዳድር ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


ጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር  ኢኤአ/ፍፋግ/ግጨ-012/2017

 

ተቋማችን የቢሮ ስም እና አድራሻ (ታፔላ) ሥራ አቅርቦትና ገጠማ እና Fire Extingusher & Installation Service በግልጽ ጨረታ አወዳድር ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

 

ሎት

 የዕቃው ዓይነት

የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO)

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

1.

የቢሮ ስም እና አድራሻ (ታፔላ) ሥራ አቅርቦትና ገጠማ

100,000.00

ጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት

ጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት

2.

Fire Extingusher & Installation Service

30,000.00

 

ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት

ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት

 

  1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
  2. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ ኮሜርስ ፊት ለፊት በሚገኘው ንብ ባንከ 10ኛ ፎቅ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መስሪያ ቤት ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል በመምጣት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ አካውንት ቁጥር 1000068699332 በመክፈል ሶፍት ኮፒ በኢሜይል አድራሻቸው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. አድራሻ፡- ሜክሲኮ ኮሜርስ ፊት ለፊት በሚገኘው ንብ ባንከ ዋናው መስሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪከ አገልግሎት ዋናው መስሪያ ቤት ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ከፍል በስልከ ቁጥር 011-126-66- 05/011-156-01-48 ይደውሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና "ETHIOPIAN ELECTRIC UTILITY" በሚል መሆን ይኖርበታል።
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባይገኙም) በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  7. ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ  ኤሌክትሪክ  አገልግሎት

 

Save Tender