የቃሊቲ አዲስ አሽ/ብቃ/ማረጋገጥ/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2017 ዓ.ም ለፅ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአ.አ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቃሊቲ አዲስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የቃሊቲ አዲስ አሽ/ብቃ/ማረጋገጥ/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2017 ዓ.ም ለፅ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን ማለትም፣
ሎት 1. አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች፣
ሎት 2. የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች፣
ሎት 3. የደንብ ልብስ
ሎት 4. የፅዳት ዕቃዎች፣
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በመስኩ የተሰማሩ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የኢፌድሪ የገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የተ.እ.ታ ተመዝጋቢዎች ለመሆናቸው ኮፒ ማስረጃ እና Tin No ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/ አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ቢሮ ቁጥር 21 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ /Financial/ ሰነድ፣ እንዲሁም አስፈላጊ ቴክኒካል ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በመለየት ኦርጂናልና ኮፒውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 04 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን መ/ቤቱ በሰጣቸው ሰነድ ላይ መሙላት እና በእያንዳንዱ የመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ፊርማ በመፈረም የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና እንዲቀርብ ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታ ከመክፈቻ ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5፡00 ሰአት ላይ ይከፈታል፣፣
- ተጫራቾች ውሉን ሲዋዋሉ ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0904159873/ 0913149064 ደውሎ መጠየቅ ወይም ቃሊቲ ማሰልጠኛ ግቢ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድ ና ቁጥጥር ባለስልጣን ቃሊቲ አዲስ ቅ/ጽ/ ቤታችን ቢሮ ቁጥር 04 በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአ.አ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቃሊቲ አዲስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
