በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መ/ጤና ቢሮ የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ ቁሳቁሶች እና የተለያዩ አገልግሎቶችን በጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መ/ጤና ቢሮ የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መ/ጤና ቢሮ የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ ቁሳቁሶች
- የፅህፈት መሳሪያ (ሎት 1)
- የፅዳት ዕቃዎች (ሎት 2)
- ደንብ ልብስ (ሎት 3)
- ኤሌክትሮኒክስ (ሎት 4)
- ፈርኒቸር (ሎት 5)
- የህንፃ መሳሪያ (ሎት 6)
- የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች (ሎ ት 8)
- የትራንስፖርት አገልግሎት (ሎት 9)
በጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት
- አቅራቢው የተሠማራበትን የሥራ ዘርፍ የሚገልፅ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin No/
- ከተሰማራበት ዘርፍ ጋር በተያያዘ ስለተሰማራበት የሙያ ዘርፍ አቅራቢነት በሚመለከተው አካል የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (የቀረበው ማስረጃ በኦንላይን እንዲታይ የቀረበ ከሆነ በኦንላይን የ egp ፖርታል ላይ ካለው ጋር ተናባቢ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጽ መረጃዎችን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚያቀርቡት አጠቃላይ
- የጽህፈት መሳሪያ (ሎት 1) ብር 8,000
- የፅዳት እቃዎች (ሎት 2) - ብር 5000
- ደንብ ልብስ (ሎት 3) ብር 6,000
- ኤሌክትሮኒክስ (ሎት 4) ብር 10,000
- ፈርኒቸር (ሎት 5) ብር 10,000
- የህንፃ መሳሪያ (ሎት 6) ብር 3,000.00
- የመኪና መለዋወጫ እቃዎች (ሎት 8 )ብር 5,000.00
- የትራንስፖርት አገልግሎት (ሎት 9) ብር 3,500.00
- ሀ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም
- ለ/ በማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት የቀረበ ዋስትና ወይም
- ሐ/ በሲፒኦ ወይም በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼከ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ ህጋዊ ማህተም ያለው ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ለውል ማስከበሪያ የሚሆን በቂ ዋስትናና ለዋስትና ሊበቁ የሚችሉ ማስያዣዎች 10% ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነድን ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመያዝ ሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግዢ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል ቀርበው በመክፈል ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የፋይናንሻልና ቴክኒካል ሠነድ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በተለያዩ ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል፡፡ በመክፈቻው ዕለት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች አለመገኘታቸው የጨረታ መክፈት ሂደትን አያስተጓጉልም::
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል::
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ፅህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት እቃዎች የደንብ ልብስ የህንፃ መሳሪያ ናሙና ማቅረብ እና የፈርኒቸር ናሙና በፎቶ ከመወዳደሪያ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን ንብረቶች ሚ/አ/ጤ/ሳ/ኮሌጅ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0473360763 መጠቀም ይችላሉ፡፡
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መ/ጤና ቢሮ የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
