የእድግት በህብረት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
እድገት በህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የእድግት በህብረት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1 አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ ሎት 2 የደንብ ልብሶች፣
ሎት 3 አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
ሎት 5 የተለያዩ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 6 ልዩ ልዩ መሣሪያዎች፣
ሎት 7 የህትመት ሥራዎች፣ ሎት 8 የኤሌክትሪክ እቃዎች ጥገና፣
ሎት 9 ግንባታና ጥገና ሥራ፣
በዚህ መሰረት በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ -
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር አጠናቃችሁ የከፈላችሁ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፤ የቫት ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለሎት 1. 1,000.00፤ ለሎት 2. 1,000.00፣ ለሎት 3. 1,000.00፣ ለሎት 4. 1,000.00 ለሎት 5. 2,000.00 ለሎት 6. 1,000.00 ለሎት 7. 500.00 ለሎት 8.1,000.00 ለሎት 9. 2,000.00 በባንክ በተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የምትችሉ፡፡
- ለጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እድገት በህብረት ቅድመ የአንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ረዳት ፋይናንስ ቢሮ በግንባር በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የምትጫረቱትን እቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የምታቀርቡትን ዋጋ ዝርዝር በሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ ሞልታችሁ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ በሥራ ሰዓት ለዚሁም በተዘጋጀ ሳጥን እድገት በህብረት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ረዳት ፋይናንስ ቢሮ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያው በወጣበት በ10ኛው ቀን 10፡00 (አስር) ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ በ11ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት እድገት በህብረት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ረዳት ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን የበዓል ቀን ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ለእያንዳንዱ ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ዋስትና ጊዜ ከአንድ ዓመት በላይ የዋስትና ጊዜ መስጠት አለበት።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- ለገሀር የዱሮ ፀረ-ሙስና ጀርባ /አዋሽ ባንክ ጀርባ/ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አጠገብ
ስልክ ቁጥር :- 011-5-58-36-58/011-5-58-18-13
እድገት በህብረት ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
